Home ዜና አየር መንገዱ ለቦርድ አባላቱ ሽኝት አደረገ

አየር መንገዱ ለቦርድ አባላቱ ሽኝት አደረገ

አየር መንገዱ ለቦርድ አባላቱ ሽኝት አደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቀድሞ የአየር መንገዱ ቦርድ አባል ለነበሩት ክቡር የኢ.ፌ.ዲ. ሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሽኝት መርሐ ግብር አካሄደ።


በዚህ የሽኝት መርሀግብር ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ሌ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣ የቦርድ አባላት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የአመራር አባላት ተገኝተዋል።


በመርሀግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ባስተላፉት መልዕክት አየር መንገዱ አህጉራዊ መሪነቱን እና አለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል እንዲሁም እንደወትሮው ሁሉ የጥንካሬ የእድገት እና የአዳዲስ ዕመርታዎች ተምሳሌት ሆኖ እንዲዘልቅ ክቡር ፕሬዝደንት በቦርድ አባልነታቸው ላበረከቱት አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበዋል።


በተመሳሳይም አየር መንገዱን በቦርድ አባልነት ያገለገሉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ወሮ ያስሚን ወሀብረቢ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።