አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በአለም ምርጥ የትምህርት ተቋም  በ808ኛ ደረጃ ተቀመጠ

Date:

የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አሰጣጥ ማዕከል በዘንድሮ እትሙ 21,462 የትምህርት ተቋማትን ደረጃ የሰጠ ሲሆን  ከነሱ መካከል ከፍተኛ ደረጃ ላይ የወጡት ግሎባል 2000 ዝርዝር ውስጥ አካቷል።

በዚህ ዝርዝር ወስጥ ስድስት የኢትየጵያ ዩንቨርስቲዎች ተካተዋል።

ማዕከሉ  ዩኒቨርሲቲዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ለመመዘን 74 ሚሊዮን የዳታ ነጥቦችን በአራት ዋና ዋና መለኪያዎች ላይ ተመስርቶ ገምግሟል፤ እነርሱም፡-
👉የትምህርት ጥራት (25%)
👉ቅጥር (ተቀጣሪነት) (25%)
👉የፋኩልቲዎች ጥራት (10%)
👉የምርምር አፈጻጸም (40%) ናቸው።

በዚህ ደረጃ የኢትዮጵያዎቹ;

⭐️አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከኢትዮጵያ አንደኛ ከአለም በ808ኛ

⭐️ጎንደር  ዩንቨርስቲ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ከአለም 1607ኛ

⭐️ጅማ ዩንቨርስቲ  ከኢትዮጵያ 3ተኛ ከአለም 1701ኛ

⭐️መቐሌከኢትዮጵያ 4ተኛ ከአለም 1757ኛ 

⭐️ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ከኢትዮጵያ አምስተኛ ከአለም 1803ኛ

⭐️እንዲሁም ሀረማያ ዩንቨርስቲ ከኢትዮጵያ ስድስተኛ ከአለም 1903ኛ ደረጃን አግኝቷል።

ለአስራ አራተኛ ተከታታይ ዓመት፣ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ደረጃነቱን አስጠብቋል።  የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም  እና የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል ። የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

ፕሪንስተን፣ የፔንስልቬኒያ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሎምቢያ፣ ዬል እና የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ከ ስድስት አስከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘዋል።  እነዚህም ሁሉም የግል የአሜሪካ ተቋማት ናቸው። በሌላ በኩል ቻይና  346 ዩኒቨርሲቲዎችን በ2000 ዝርዝር ወስጥ በማካታት ብዛት ያለው ተቋም በማካታት አንደኛ ሆናለች።

ከአፍሪካ የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ዩንቨርስቲ ከአለም 271ኛ ደረጃ ከአፍሪካ ደግሞ የአንደኛ ደረጃን አግኝቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...