በነጩ ቤተ -መንግስት ለዘገባ የተገኘችውን አፍሪካዊት ጋዜጠኛ ቆንጆ ነሽ በማለት አድናቆታቸውን የገለጹት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት መነጋሪያ ሆነዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዴሞክራቲከ ሪፐብሊክ ኮንጎንና ረዋንዳን ለማስታረቅ በተሰናዳው ስነ-ስርዓት ላይ በነጩ- ቤተ መንግሰት ለዘገባ የተገኘችውን አንጎላዊት ጋዜጠኛ ሃርያና ቬራስን ነው ቆንጆ ነሽ ሲሉ ያደነቋት፡፡
እንዳንች ያሉ ቆነጃጀት ጋዜጠኞች ቢበዙ እንዴት መልክም ነበር ሲሉም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
“ይህን ማለቴ ትክክል ላይሆን ይችላል” ቢሆንም “በጣም ውብ ናት” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
