የታሊባን መንግስት ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ በእሁድ በሬክተር ስኬል 6.0 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 1ሺ 411 ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል።
የዩኤስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ (USGC)ዛሬ ረቡዕ እንዳለው ከሆነ ደግሞ አዲስ 5.2 በሬክተር የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በተመሳሳይ ቦታ ላይ አጋጥሟል ብሏል። የመሬት መንቀጥቀጡ መነሻው ከጃላላባድ በስተሰሜን ምስራቅ 34 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሲሆን 12:29 ላይ በ10 ኪሜ ጥልቀት ጥልቀት ላይ መከሰቱ ገልጿል።
ባጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ ሰፊ ችግር ውስጥ ለገባችው አፍጋኒስታን አለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥያቄ በቀረበበት በአሁኑ ሰዓት ዩናይትድ ኪንግደም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ቀይ መስቀል ለተጎዱት አፍጋኒስታናውያን የጤና እንክብካቤ እና የአደጋ ጊዜ አቅርቦቶችን ለማድረስ 1 ሚሊየን ፓውንድ መመደባቸዎ ታውቋል። ህንድ በበኩሏ 1ሺ የቤተሰብ ድንኳኖችን ወደ ካቡል እንዳስረከበች እና 15 ቶን ምግብ ወደ ኩናር እያጓጓዘች መሆኗን አስታውቃለች።
