ኢሚሬቶች ገንዘባቸውን በወርቅ እየለወጡ ነው

Date:

•  ባንኮች ለደንበኞች ወርቅ ገዝተው እያስቀመጡ ነው

የቅንጦት አለም ተብላ የምትታወቀውና በአስደናቂ የከተማ ቱሪዝምና ቴክኖሎጂ የበለፀገችው የተባበሩት አረብ ኤሚሬት፣ በባንክ ከሚቀመጥ ሂሳብ ይልቅ ወርቅን ገዝቶ ወደ ማስቀመጥ ፊቷን አዙራለች።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ባንኮችም ለደንበኞቻቸው ወርቅ ገዝተው እያስቀመጡ እንደሆነ ገልፍ ኒውስ በዘገባው አትቷል።

ባንኮች ለደንበኞቻቸው ደህንነትና ምቾት በሚል ለአብዛኞቹ ደንበኞቻቸው ገንዘባቸውን በወርቅ እያስቀመጡ ሲሆን፤ ለዚህም ምክንያቱ  ወርቅ – ጊዜ የማይሽረው ፣ የሚጨበጥና የታመነ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

ለብዙ የአገሪቱ  ባለሃብቶች የገንዘብ መቆጠቢያ መሳሪያ እየሆነ መምጣቱም  ነው የተገለጸው፡፡

ወርቅ አለም ላይ እየተስተዋለ ያለውን ተለዋዋጭ ምንዛሬና የኑሮ ውድነት እንዲሁም ላልተረጋጋው የሉላዊ  ግብይት ስርዓት፣ ከባንክ የቁጠባ ሂሳቦች የበለጠ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ አማራጭ ሆኖ እየታሰበ መምጣቱ ተዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል፣ በተባበሩት አረብ ኤሚሬት የውጭ ሀገር ባለሀብቶች በወርቅ ንግድ ላይ መሰማራታቸው ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...