ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ 27 የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት ፈፀመች

Date:

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ላደረሱት የቦንብ ጥቃት ለመበቀል ለስድስተኛ ጊዜ ጥቃት እየፈፀመ መሆኑን የኢራን መንግስት ሚዲያ ዘግቧል።

በእስራኤል እና በአካባቢው በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ “ሰፋ ያለ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላን” ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።

27 የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች፣ እንዲሁም የእስራኤል ቴል ኖፍ አየር ማረፊያ፣ በቴል አቪቭ የሚገኘው የእስራኤል ጦር አዛዥ ዋና ፅህፈት ቤት ሃኪሪያ እና በተመሳሳይ ከተማ በሚገኝ አንድ ትልቅ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ላይ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ገልጿል።

የኢራን ሃይሎች “የተለየ እና ከባድ የበቀል እርምጃን በተከታታይ” እንደሚተገብሩም አክለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...