ኢትዮጵያ እና ቱርክሜኒስታን ትብብራቸውን ለማጠናከር ተወያዩ

Date:

የኢትዮጵያ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ሥሜ ከቱርክሜኒስታን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አክመድ ጉርባኖቭ ጋር የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ሰለማሳደግ መክረዋል፡፡

ከሦስተኛው የተባበሩት መንግሥታት በማደግ ላይ ያሉ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ጉባኤጎን ለጎን የተደረገው ውይይት፦

በትራንስፖርት፣
በዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ፣
በባሕል እና
በሰብዓዊ ጉዳዮች ትብብርን ማስፋት ላይ ያተኮረ ነበር።

ሁለቱ ወገኖች ግንኙነቶችን በማጠናከር ለዘላቂ ልማት እና ለቀጣናዊ ውህደት የጋራ እርምጃዎችን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ማረጋገጣቸውን የቱርክሜኒስታን ሚዲያ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ልዑካን በታህሳስ 2025 በቱርክሜኒስታን ሊካሄድ የታቀደውን ዓለም አቀፍ የሰላም እና መተማመን መድረክ እንደሚደግፍም ገልጿል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...