ኢትዮጵያ እና ኬንያ የድንበር ንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና የኬንያ የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ካቢኔ ሲክሬተሪ ሊ ኪንያንጂዩን በትናንትናው ዕለት የድንበር ንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ እ.ኤ.አ ሚያዚያ 17 ቀን 2025 በኬንያ ሞምባሳ የተደረሰበት ስምምነት አካል መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ አክለውም በሁለቱ ጎረቤት አገሮች መካከል ለረጅም ጊዜ የወዳጅነት እና የሁለትዮሽ ትብብር ታሪክ ውስጥ ጉልህ ምዕራፍ የሚኖረው ነው ብለዋል።

አክለውም የንግድ እንቅፋቶችን በመቀነስ አነስተኛ መጠን ያለው ድንበር ተሻጋሪ ንግድን የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በአሁኑ ጊዜ አብዛኛዎቹን መደበኛ ያልሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች በተለይም ለሴቶች እና ወጣቶች ግልጽና ሊገመት የሚችል ማዕቀፍ የሚፈጥር መሆኑንም ጠቁመዋል።

ስምምነቱ ወደ ሙሉ ትግበራ ሲገባ የንግድ ዕድሎችን የሚያሰፋ ሲሆን የሁለቱ ሃገራት መንግስታትና የግሉ ዘርፍ በጠንካራ ቅንጅት መስራት ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል። 

በተጨማሪም ስምምነቱ የጉምሩክ አሠራሮችን ቀላል በማድረግ እና ሰነዶችን በማስማማት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ህጋዊ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ተመላክቷል።

የኬንያ ልኡካን ቡድን በቆይታቸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የወጪ ንግድ ማዕከል መጎብኘታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...