ኢትዮጵያ እና 29 ሀገራት የዓለም አቀፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትብብር መሰረቱ

Date:

በሻንጋይ እየተካሄደ ባለው የ2026 የዓለም አቀፍ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉባኤ (WAIC) ዋዜማ ላይ ሐሙስ ዕለት በተከናወነው ሥነ-ሥርዓት፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ስምምነቱን በኢትዮጵያ ስም ፈርመዋል።

በጠቅላላው 29 ሀገራት የፈረሙት የዚህ አዲስ ነፃ መንግሥታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት የማቋቋሚያ ስምምነት ላይ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በሀገራቸው ስም የፈረሙ ሲሆን፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ታድመዋል።

ዋና መሥሪያ ቤቱን በሻንጋይ የሚያደርገው ይህ ድርጅት የተመድ ቻርተር ዓላማዎችን የሚያከብር፣ ለሰፊ ምክክርና ለጋራ ጥቅም በጋራ ለማበርከት ቁርጠኛ የሆነ እንዲሁም ሰውን ማዕከል ያደረገ አካሄድን የሚከተል ነው መባሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ድርጅቱ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ ዓለም አቀፍ ትብብርንና አስተዳደርን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን፥ ይህም የኤአይ (AI) ልማት ለመላው የሰው ልጅ ጠቃሚ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ በሆነ አቅጣጫ እንዲጓዝ ለማድረግ ታስቦ የተመሰረተ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...