ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ለሚሰነዘርባት ዘለፋ ምላሽ የመስጠት ፍላጎት የላትም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ

Date:

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ከጎረቤት ሀገራት ለሚሰነዘርባት ዘለፋዎች ምላሽ የመስጠት ፍላጎት የላትም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ግንቦት 21 2017 ዓ.ም በወቅታዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረውን ሳምንታዊ መግለጫ፤ በቃል አቀባዩ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በኩል ሰጥቷል።

ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሁልጊዜም የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር እንደምትሰራ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራን የነፃነት ቀን ግንቦት 16 ባከበሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያን በተመለከተ ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል።

ይህ ንግግራቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያንን ያስቆጣ ሲሆን፤ የተለያዩ ሀሳቦችም እየተሰነዘሩበት ቆይተዋል።

ይህንን በተመለከት ጥያቄ የቀረበለት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በቃል አቀባዩ በኩል ምላሽ የሰጠ ሲሆን፤ ቃል አቀባዩ “ኢትይዮጵያ ለሚሰነዘሩባት ዘለፋዋች ምላሽ የምስጠት ፍላጎት የላትም” ብለዋል።

ኢትዮጵያ የተረጋጋ አካሄድን የምተከተል ሀገር መሆኗን የገለጹት አምባሳደር ነብያት፤ “ከዚህ ቀደምም ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት በመሪዎቹ ደረጃ ተገቢ ያልሆኑ ክሶችና ዘለፋዋች ደርሶባት ያውቃል” ሲሉ ገልጸዋል።

“ኢትይጵያ ግን እንደዚህ ያለ እንካ ሰላምትያ ዉስጥ ሳተገባ በሰከነ ዲፕሎማሲ መንገድ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የምትቀጥል ነው የሚሆነው” ብለዋል።

በሌላ በኩል የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሥም በመጠቀም ‘ወደ ውጪ እንልካለን’ የሚሉ አካላት መኖራቸውንም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል

ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ጋር በተያያዘ ከማይናማር ከ700 በላይ ዜጎችን መመለስ መቻሉንም አምባሳደሩ በሳምንታዊ መግለጫቸው ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ መንግሥት በዚሁ ሁሉ ጥረት እያደረገ ባለበት በዚህም ወቅት፤ ይህንን የሕገ-ወጥ መንገድ ተከትሎ የሚሄዱ ዜጎች አሁንም መኖራቸውን እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

‘ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕጋዊ ፍቃድ አለኝ’ በማለትና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሥም በመጠቀም ሀሰተኛ ማስረጃ በማስራጨት ‘ወደ ውጪ እልካለሁ’ የሚሉ ሐሰተኛ ግለሰቦች መኖራቸውን ሕዝብ ሊረዳ ይገባል ብለዋል።

ይህ ሀሰተኛ ማስረጃ በተለያየ ማህበራዊ ሚዲዎች እየተሰራጨ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሩ፤ ስህተት መሆኑን ሕዝብ ሊረዳ እንደሚገባም አሳስበዋል።

“የሕገ-ወጥ መንገድ የሚወስዱ ደላሎች ሰንሰለታቸው ረጅም ርቀት ያለው ቢሆንም፤ ርምጃ ለመውሰድ ሥራዎች ቢሰሩም አሁንም ችግሩ አልተቀረፈም” ሲሉም ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...