ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በቀይ ባሕር ላይ አካታች ትብብርን ቢያበረታታ ተጠቃሚ ይሆናል አለች

Date:



ኢትዮጵያ ከመጋቢት 18 እስከ 19 በብራዚል በተካሄደው በመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ የብሪክስ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ልዩ መልዕክቶች ስብሰባ ላይ ተሳትፋለች፡፡ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር በመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ ቀጣና ያሉ ግጭቶች እና ሰብዓዊ ቀውሶች ኢትዮጵያን እንደሚያሳስቧት ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ለሱዳን ግጭት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለማምጣት ጥረት እያደረገች እንደሆነ ያከሉት አምባሳደሩ፤ አቅም ያላቸው የብሪክስ አባል ሀገራት ለሱዳን ሰብዓዊ ቀውስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር እና በሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ የምትገኝ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ሀገር መሆኗንም አስታውሰው፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በቀይ ባሕር እና ሕንድ ውቅያኖስ ላይ አካታች ዓለም አቀፋዊ ትብብርን ቢያበረታታ ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።

ስብሰባው ባወጣው የጋራ መግለጫ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሰሜን አፍሪካ የቀጠሉ ግጭቶች አሳሳቢ እንደሆኑ አበክሮ መግለፁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...