ኢትዮጵያ የብሪክስ ቡድንን ለመቀላቀል ያቀረበቸው ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

Date:

መንግሥት ከ180 ቢሊዮን ብር በላይ ቀጥታ ብድር መውሰዱ ታወቀ

በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት ከፍተኛ የበጀት እጥረት ገጥሞት የነበረው መንግሥት፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወሰደው ቀጥታ ብድር (Direct Advance)፣ ከ180 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ ታወቀ፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝና የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ባስከተሉት የኢኮኖሚ አለመረጋጋት፣ ወጪው በመጨመሩ ምክንያት ከፍተኛ የበጀት እጥረት ውስጥ ገብቶ የነበረው መንግሥት፣ ከብሔራዊ ባንክ በከፍተኛ መጠን መበደርን ጨምሮ በርካታ የገቢ ማስገኛ መንገዶችን ሲጠቀም እንደነበር ይታወሳል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥት በቀጥታ (ገንዘብ በማተም) ሲያበድር የቆየ ሲሆን፣ በተጠናቀቀው ሙሉ የበጀት ዓመት የሰጠው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ከ180 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን ሪፖርተር የተመለከታቸው ሰነዶች ያረጋግጣሉ፡፡ ገንዘቡን ከሚያበድረው ብሔራዊ ባንክና ለመንግሥት ሥራ ማስፈጸሚያ ከሚበደረው የገንዘብ ሚንስቴር የሪፖርተር ምንጮች የተገኘው መረጃም ይህንን የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ ከብሔራዊ ባንክ በተገኘው መረጃ መሠረትም የገንዘብ መጠኑ በአሥር ቢሊዮን ብር ከፍ ሊል እንደሚችል ነው፡፡ የበጀት ዓመቱ ከተጀመረ በኋላ የመጀመርያው ሩብ ዓመት እኪጠናቀቅ ድረስ 60 ቢሊዮን ብር ቀጥታ ብድር መወሰዱን፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት አመላክቶ ነበር፡፡ ከዚህ 60 ቢሊዮን ብር ጋር ባለፉት ጥቂት ዓመታት ተጠራቅሞ የነበረው 236.5 ቢሊዮን ብር በቀጥታ ብድር የተገኘው ገንዘብ ወደ ረዥም ጊዜ ቦንድ በጥቅምት ወር ተቀይሮ እንደነበርም፣ መገንዘብ ሚኒስቴር ሁለተኛው ሩብ ዓመት የብድር መግለጫ ሪፖርት ላይ ተካቶ ነበር ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ የብሪክስ ቡድንን ለመቀላቀል ያቀረበቸው ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

15ኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው ብሪክስ ቡድኑን በሚያሳድግበት ሁኔታ ላይ ሲወያይ ቆይቶ አዳዲስ አባላትን ለመቀበል ወስኗል፡፡ የታዳጊ ሀገራት ኢኮኖሚን ለማሳደግ ዓላማው እንደሆነ የሚነገረው ብሪክስ፣ በጆሃንስበርግ ከተማ እያካሄደ ባለው ዓመታዊ ጉባኤው ዋና አጀንዳ የነበረውን የአባላቱን ቁጥር ማብዛት ላይ መክሮ ስድስት ሀገራት ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ፈቅዷል፡፡ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የመሰረቱት ብሪክስ፤ ኢትዮጵያ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ ግብፅ፣ አርጀንቲና እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን የቡድኑ አባል ሀገራት አድርጓል። አዳዲሶቹ አባል አገራት ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ከጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀላቀሉ የጉባኤው አስተናጋጅ የሆነችው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪልራማፎዛ ተናግረዋል፡፡

ዋን ኤም.አር.ኦ አይሮፕላን የመጠገን ፈቃድ አገኘ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋን ኤም.አር.ኦ ለተሰኘ የግል ተቋም የመጀመሪያ የሆነውን አይሮፕላን የመጠገን ፈቃድ ዛሬ ነሐሴ 15/2015 ሰጥቷል፡፡ በ2013 የቢዝነስ ፈቃድ አውጥቶ የተቋቋመው ተቆሙ ዛሬ የጥገና ፈቃድ ሰርትፊኬት ለማግኘት የበቃው፤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባዘጋጃቸውን አምስት ዓለም አቀፍ መስፈርቶች ማለትም pre-application, formal applications, document evaluation, demonstration and inspection መሰረት ተመዝኖ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ነው ተብሏል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለዚህ ተቋም የሰጠው የጥገና ፈቃድ ቦይነግ 737 ክላሲክና ቦይንግ 737 ኔክስት ጄኔሬሽን የተባሉ ዘመናዊ አይሮፕላኖችን ለመጠገን የሚያስችል እንደሆነ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ሰርተፍኬቱን የተረከቡት የዋን ኤም.አር ኦ. የጥራት ማረጋገጫና ደህንነት ማናጀር አንዱአለም ስለሺ፤ ድርጅታቸው በአሁን ሰዓት ናይጄሪያ ላይ መሰረት አድርጎ በምዕራብ አፍሪካ ለሚገኙ የግል ኦፐሬተሮች የጥገና አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ በምዕራብ አፍሪካም ሰፊ የጥገና ፍላጎት መኖሩን ተናግረዋል፡፡ ድርጅታቸው በቀጣይም በኢትዮጵያ የጥገና ሀንጋር በመገንባት የግል አየር መንገዶች እየገጠማቸው ያለውን ከፍተኛ የአይሮፕላን መጠገኛ ሀንገር ችግር ለመቅረፍ እንዳቀደ ገልጸዋል። የአይሮፕላን ጥገና ለመገንባት ዋንኛ ችግር የውጭ ምንዛሪ እንደሆነም አበክረው ተናግረዋል፡፡  አያይዘውም፤ ወደፊት በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ኢንቨስትመንት “መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግልን አምናለሁ።” ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነባው ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ይፋ ተደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከቻይናው ኤፍ ኤች ኢ ሲ ኩባንያ ጋር በሽርክና የሚያስገነባው ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ይፋ ተደርጓል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ለዚህ ፕሮጀክት የሚሆን መሬት በወቅታዊ የሊዝ ዋጋ አስልቶ ያቀረበ ሲሆን፤ የቻይናው ኤፍ ኤች ኢ ሲ ኩባንያ ደግሞ ወቅቱ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ፣ ፋይናንስና ግብዓት በማቅረብ ግንባታውን የሚያካሄድ ይሆናል ተብሏል። ጎተራ አካባቢ የሚገነባው ይህ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን፤ ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የሚገነባ መሆኑም ተነግሯል፡፡ በውስጡም ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚና የንግድ ዞን፣ የትምህርት እና የባህል ዞን፣ የፋይናንስና ቢዝነስ ዞን እንዲሁም ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ዞንን ያካተተ መሆነን ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ፕሮጀክቱ የአዲስ አበባ ከተማን ሚና በማላቅ ለንግድ እና ተያያዥ ጉዳዮች ወደ ከተማይዋ የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎችን ቁጥር በመጨመር አለም አቅፍ ሚናዋ እንደሚያጎላ ታምኖበታል፡፡

ግዕዝ ባንክ ተቋርጦ የነበረውን የአክሲዮን ሽያጭ ለመቀጠል ጥሪ አቀረበ

በምስረታ ሂደት ላይ የሚገኘው ግዕዝ ባንክ አ.ማ በሰሜኑ ጦርነት ተቋርጦ የነበረውን የአክሲዮን ሽያጭ ለመቀጠል ጥሪ አቅርቧል። ባንኩ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የአክሲዮን ሽያጭ ለመቀጠል እንዲሁም፤ የአክስዮን ሽያጩ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ ለባለ አክሲዮኖች አና ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በመጋቢት ወር 2012 በምስረታ ሂደት ላይ እያለ በተከሰተው የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የተቋረጠው የግዕዝ ባንክ አክሲዮን ሽያጭ፤ በወቅቱ የነበረውን የመመስረቻ ካፒታል  500 ሚልየን ብር ለማጠናቀቅ ከጫፍ ደርሶ እንደነበር ተገልጿል፡፡ በጦርነት ምክንያት የአክስዮን ሽያጭ እንቅስቃሴው በመቆሙ፤ የባንኩን ምስረታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዳይከናወን ከፍተኛ መስተጓጎል ደርሶበታልም ተብሏል፡፡ የሰላም ስምምነቱ ተከትሎ ተስጓጉሎ የነበረውን የአክስዮን ሽያጭ እንደ አዲስ በማነሳሳት በዚህ ወቅት ከ13 ሺሕ 800 በላይ የአክስዮን ገዢዎች መካከል1.8 ቢልየን ብር የተፈረመ መሰብሰቡን የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ቶማስ ሀይሉ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ  ዘመናዊ ኢንዱስትሪን  ለመፍጠር በምርምርና ጥናት መታገዝ እንደሚገባ ተገለፀ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ኢንዱስትሪን ለመፍጠር በምርምርና ጥናት የታገዙ ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ገለጹ። የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ያሉበትን ክፍተቶች የሚለይበትና ያለውን አቅም ማጠናከር ላይ ትኩረቱን ያደረገ አውደጥናት ተካሒዷል፡፡ ሥራ አስፈፃሚው ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ የተሻለ ኢንዱስትሪ ለመፍጠር ከአርባ ዓመታት በላይ በርካታ የማማከር ስራዎችን የሰራ ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ከ600 በላይ ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ እንዲፈጠሩ ምክንያት የሆነውን ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎትን በማጠናከር ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ በማማከርና በስልጠና ኢንዱስትሪዎችን የሚያግዝ ግዙፍ አፍሪካዊ ተቋም መፍጠር ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑም በአውደ ጥናቱ ላይ ተነስቷል። በአውደ ጥናቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ምሁራን  ተገኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በሚያካሂድባቸው ቦታዎች ሁሉ እሳተፋለሁ

በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ...

በሲዳማ ክልል ከ62% በመቶ በላይ የሚታረሰው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነዉ

በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚታየው የምርታማነት ማነቆ በዋናነት የመሬት አሲዳማነት...

የኢትዮጵያ እዳ እና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባ ሳይገኙ ቀሩ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እዳ እና...

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት የአፍሪካ-ሕንድ...