ሁለቱ ተቋማት ያደረጉት ይህ አጋርነት ደንበኞች ዘመናዊ የፋይበር ብሮድባንድ ኢንተርኔትና የሞባይል ዳታ ጥቅሎችን በመጠቀም የተለያዩ የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ የመዝናኛ ቻናሎችን በጥቅል (package) አማራጭ እንዲያገኙ ያስችላል።
ይህ አዲስ አገልግሎት የኢትዮ ቴሌኮምን ፈጣን የኢንተርኔት መሰረተ ልማት እና የዲኤስቲቪን ተወዳጅ የመዝናኛ ፕሮግራሞች በማጣመር ለተጠቃሚዎች ምቹ እና ዘመናዊ የመዝናኛ ልምድ ያቀርባል ተብሏል።
ደንበኞች ዘመናዊ የፋይበር ብሮድባንድ ኢንተርኔት እና የሞባይል ዳታ ጥቅሎችን በመጠቀም የተለያዩ የዲኤስቲቪ ይዘቶችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
ተጠቃሚዎች እንደ ፍላጎታቸው የተለያዩ ጥቅሎችን መግዛት ይችላሉ፤ እነዚህም የዲኤስቲቪ ጎጆ፣ ቤተሰብ፣ ሜዳ፣ ሜዳ ፕላስ እና ፕሪሚየም ተወዳጅ የሀገር ውስጥ ጥቅሎችን እና እስከ 35% ቅናሽ የተደረገባቸውን ዓለም አቀፍ ቻናሎችም ማግኘት ይቻላል ብሏል።
