ኢጋድ ሱዳን በድርጅቱ ሙሉ ተሳትፎዋን ለመቀጠል ያሳለፈችውን ውሳኔ ተቀበለ

Date:

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሱዳን ሪፐብሊክ በድርጅቱ ሙሉ ተሳትፎዋን ለመቀጠል ያሳለፈችውን ውሳኔ በደስታ እንደሚቀበል አስታወቀ።

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ የሱዳን ወደ ኢጋድ የመመለስ ውሳኔ ለቀጣናዊ አንድነት፣ ትብብር እና የጋራ ርምጃ አዲስ ቁርጠኝነትን ያሳያል።

የኢጋድ መስራች አባል የሆነችው ሱዳን ወደ ድርጅቱ መመለሷ የተቋሙ የጋራ ቀጣናዊ ተግዳሮቶችን የመፍታት ችሎታን እንደሚያሳድግ አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት የኢጋድ ሊቀመንበር የሆኑት የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህ ላደረጉት ጥረት አመስግነው÷ በውይይት እና የጋራ መግባባትን በመፍጠር በኩል ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል።

ድርጅቱ ሀገሪቱ አሁን ላይ ለገጠማት ተግዳሮቶች ሰላማዊ መፍትሄዎችን በመደገፍ እና ቀጣናዊ መረጋጋትንና ልማትን ለማሳደግ በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ንባብ ለህይወት!” ታላቅ የንባብ ሳምንት እና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የንባብ ለህይወት...

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚልዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ እና ከ2...

የቶዮታ ኮሮላ መኪና በኤሌክትሪክ ሊመጣ ነዉ

የዓለማችን ግዙፍ የመኪና አምራች የሆነው ቶዮታ፤ እንደ ቴስላ እና...

ኢራንን ለመምታት የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከምድሯ ይነሱ እንደነበር እሥራኤል ይፋ አደረገች

የእሥራኤል መከላከያ ሚንሥትር እሥራኤል ካትስ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች...