- ለትምህርት ቤቶች አመራርና ሰራተኞች ለቤትና ለመኪና መግዣ
የሚውል አዲስ የብድር አገልግሎት መጀመሩን ይፋ አድርጓል።
እናት ባንክ ትምህርት ቤቶች ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን የሚያገኙበትን “እናት መላ” የትምህርት ቤት ክፍያ ሥራዓትን (UNICASH) በተመለከተ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የሥራ ሃላፊዎችና ተወካዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል።
“እናት መላ” የትምህርት ቤት ክፍያ ሥርዓት ተማሪዎችን ለመመዝገብ፣ የጉዞ፣ የመጽሐፍ ግዢና የትምህርት ክፍያን በቀላሉ ለመፈጸም ያስችላል፡፡ በተጨማሪም የተማሪዎችን መረጃ ለማስተዳደር፣ የፋይናንስ ሪፖርት ለማዘጋጀት እና ከተማሪ ወላጆች ጋር ያለውን ግንኙነትን ለማሳለጥ ፋይዳው የጎላ ነው።
የእናት ባንክ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ትዕግስት አባተ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ስሜ በበኩላቸው እናት መላ የተሰኘ የትምህርት ቤት ክፍያና የተማሪ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት ባለፉት ሶስት አመታት ለትምህርት ቤቶች በማቅረብ አበረታች ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል ።ይህም ትምህርት ቤቶች አሰራራቸውን እንዲያዘምኑ ማስቻሉን አስረድተዋል።
በሌላ በኩል
እናት ባንክ ለትምህርት ቤቶች አመራርና ሰራተኞች ለቤትና ለመኪና መግዣ የብድር አገልግሎት እንደሚያመቻች ገልጿል።
እናት ባንክ ለግል የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ መምህራን እና ሌሎች ሰራተኞች የተዘጋጀ አዲስ የብድር አግልግሎት መጀመሩን ይፋ አድርጓል። የተሟላ፣ ቀልጣፋ እና ምቹ የባንክ አገልግሎት ለሁሉም ማህበረሰብ ማቅረብ አንዱ የባንኩ ስልታዊ እቅድ በመሆኑ ይህ የብድር አገልግሎት በትምህርቱ ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎችን ለመደገፍ እና ተጠቃሚ ለማድረግ የተዘጋጀ ስለመሆኑ ባንኩ አስታውቋል፡፡
ለዚህም ሁለት የብድር አይነቶችን ስለማዘጋጀቱ ጠቁሟል፤ እነዚህም:-
1- የአጭር ጊዜ ብድር ፦ (ከተበዳሪዉ ሰራተኛ ከአንድ አመት የደመወዝ መጠን ያልበለጠ)
2- የደመወዝ ቅድመ ክፍያ ብድር ፦ (በእናት ማለፊያ ዲጂታል የብድር
አገልግሎት አማራጭን በመጠቀም የሚሰጥ)
ይህን የመኪና ብድር የቤት ብድር
ለማግኘት፤ የትምህርት ተቋሙ የእናት ባንክ “ዩኒ ካሽ” የክፍያ ስርዓት ተጠቃሚ መሆን፣ የትምህርት ተቋሙ በእናት ባንክ ለ6 ወራት በተከታታይ መቆጠብ፣ ተበዳሪዉ ሰራተኛ በትምህርት ቤቱ ተቀጥሮ 6 ወር ያገለገለ መሆን፣ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ያለዉ/ያላት መሆን እና የትምህርት ተቋሙ በ”ዩኒ ካሽ” የክፍያ ስርዓት የተሻለ የገንዘብ ዝውውር ሊኖረው መገባቱ ዋና ዋና መስፈርቶች ናቸው።
ይህን የብድር አገልግሎት ማግኘት፤ ተመጣጣኝ የወለድ መጠን አነስተኛ የመያዣ መስፈርት፣ የመክፈያ አቅምን መሰረት በማድረግ የክፍያ ጊዜ አማራጮች፤ ከሚያስገኛቸው ልዩ ጥቅሞች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
