ከስሃራ በታች የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት ለሞት እንደሚዳረጉ ተገለፀ

Date:

እንደ ድርጅቱ ዓለም አቀፍ እርዳታ መቀነሱ ለብዙ አሥርት ዓመታት የህጻናት ሞትን ለመከላከል በተደረገው ጥረት የተገኘውን ውጤት የሚገታ እና ሁኔታውንም እስከመቀልበስ የሚያደርስ ነው ። የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት UNICEF በዓመታዊ ዘገባው የእርዳታ ገንዘብ ቅነሳ መዘዝ በተለይ አሁንም ከሰሀራ በታች በሚገኙ ሀገራት ከፍተኛ የሆነው የህጻናት ሞት እንዲባባስ ምክንያት መሆኑ እንደማይቀር አስጠንቅቋል።

የድርጅቱ የጤና ጉዳዮች ተባባሪ ሃላፊ ፋውዝያ ሻፊክ እንደሚሉት በጎርጎሮሳዊው በ2023 ዓም እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ህጽናት ሞት እየቀነሰ መሄዱ የተመዘገበበት ዓመት ነበር። ያም ሆኖ በዓመቱ 4.8 ሚሊዮን ህጻናት ሞተዋል። ይህም ከፍተኛ ቁጥር መሆኑን ሳይጠቅሱ አላለፉም።

ከዚህ ሌላ የእርዳታ ቅነሳው የጤና ሰራተኞች እጥረት ፣የክሊኒኮች መዘጋትን የክትባት መርሀግብር መዛባትን እና ወባን የመሳሰሉ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስፈልጉ መሰረታዊ አቅርቦቶችን እጦትም አስከትሏል። ተባባሪ ሃላፊዋ እንዳሉት በዚህ ረገድ የወባ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣባትን ኢትዮጵያን እንደምሳሌ አንስተዋል። ሀገሪቱ የምርመራ አገልግሎት ፣ ወባን ለመከላከል የሚረጩ መድኃኒቶች ፣እና የአጎበሮች እንዲሁም ለበሽታው መከላከያ የሚካሄዱ ዘመቻዎችን ለሚደግፍ እርዳታ እጥረት ተጋፍጣለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...