ከ1.8 ሚሊየን በላይ ሰዎችን የደገፈው የሰብአዊ እርዳታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

Date:

 

ዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በግጭት፣ በድርቅ፣ በቦታ መፈናቀል እና ሌሎች ሰብዓዊ ፈተናዎች የተጎዱ ከ1.8 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ የሆኑበት የሶስት ዓመት የተቀናጀ የሰብዓዊ ምላሽ ፕሮጀክት ማጠናቀቁን አሳውቋል።

ፕሮጀክቱ በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልሎች በሚገኙ 27 ወረዳዎች ውስጥ ተተግብረዋል።

ይህ አጠቃላይ ፕሮጀክት በጤና፣ በስነ-ምግብ፣ በውሃ፣ ንፅህና ፣ ኤችአይቪ፣ በህፃናት ጥበቃ እንዲሁም በህይወት ማሻሻያ ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራትን አስተባብሮ የያዘ ሲሆን፥ተጎጂ ማህበረሰቦች ከችግር እንዲያገግሙና የወደፊት የመቋቋም አቅማቸውን እንዲገነቡ አስችሏል።

በፕሮጀክቱ ከ41 ሺህ በላይ ህፃናት ለከባድ የምግብ እጥረት ህክምና አግኝተዋል ከ2መቶ9 ሺህ በላይ ህፃናት ደግሞ ለቅድመ ምርመራ እና ህክምና ተመዝግበዋል።

በተጨማሪም ከ3መቶ 53 ሺህ በላይ የህክምና ምክክሮች ተሰጥተዋል።

2ሺህ 6መቶ40 የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ያገኙ ሲሆን፥61 የጤና ተቋማትም ታድሰዋል።

በተጠገኑ የውሃ መስመሮች አማካኝነት ከ53ሺህ በላይ ሰዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ እና ተያያዥ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሆነዋል።

የዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ሀገራዊ ዳይሬክተር ካርመን ቲል እንደተናገሩት፥ “የዚህ ፕሮጀክት አላማ እርዳታ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ህፃናት ከችግር ተላቀው በህይወት ለመቆየት፣ ለማንሰራራት እና የተሻለ መፃኢ እድል ለመገንባት የሚያስፈልጓቸውን አገልግሎቶች፣ ጥበቃ እና እድሎች ማግኘታቸውን ማረጋገጥ ነው” ::

ድርጅቱ እንደገለፀው፥በአካባቢው የነበሩ የጸጥታና የተደራሽነት ፈተናዎች ሳይበግሩት ከመንግስት፣ ከሀገር ውስጥ አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ድጋፉን ሳያቋርጥ ማዳረስ ችሏል።

ዎርልድ ቪዥን አሁንም በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ከፍተኛ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት እንዳለ በመጠቆም ለህፃናት ጤና፣ ስነ-ምግብ፣ ጥበቃ እና ውሃ አገልግሎቶች ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መልካም አዲስ ዓመት!!

  ግዮን መጽሔት :-   አዲሱን የኢትዮጵያ ዓመት ስንቀበል፣ ለውዷ ኢትዮጵያችንና...

የድሬዳዋ አስተዳደር ተሿሚዎች

4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደዉ...

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተሿሚዎች

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ...

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ተሿሚዎች

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ...