“ኪሳራም ሥራ ነው” የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

Date:

የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው ከፈለኝ ሐይሉ ያሳተሙት “የቢዝነስ ሀሁ በኢትዮጵያ “ኪሳራም ሥራ ነው” የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር) በይፋ ተመርቋል።

በኢትዮጵያ ያለው የንግድ ስርዓት በዘርፉ ለተሰማሩ የንግድ አካላት በአሳሪ ቢሮክራሲና በሌሎች ምክንያቶች መታሰሩ፤ ንግድ በኢትዮጵያ እድገቱ በታሰበው ልክ እንዳይሆን አድርጎታል።

የኢትዮጵያ የንግድ ስርዓት ንግድ በማያውቁ የመንግስት ሃላፊዎች መመራቱ ዘርፉ በሚገባው ልክ እንዳያድግ ስለማድረጉ በመጽሐፉ ዙሪያ ውይይት በተደረገበት በዚሁ መድረክ ላይ ተነግሯል።

በውይይቱ የተለያዩ የፋይናንስ እና ቢዝነስ ባለሙያዎች፣ ኢንተርፕርነሮች እና በርካታ ታዳሚዎች የተገኙ ሲሆን፤ መፀሐፉ ውስጥ በተመረጡ ሃሳቦች ዙሪያ ሙያዊ እይታቸውን አጋርተዋል።

የንግድ ስርዓት፣ የፋይናንስ ፍሰት እና የግብር ስርዓት በኢትዮጵያ ያለው መልክ ከሳይንሱ እና አጠቃላይ የዘፈቀደ  አካሄዶች ያላቸው መልክ ምን ይመስላል የሚለው ተዳሶበታል።

አሐዱ ሬድዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...