ኬንያ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎቻን ሙሉ በሙሉ በጀት ሊትሸፈን ነዉ

Date:

የኬንያ መንግስት ከሚቀጥለው መስከረም 2026 ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የሚገቡ ሁሉንም ተማሪዎች ትምህርት ሙሉ በሙሉ በመንግስት በጀት እንደሚሸፈን ይፋ አደረገ።

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ አዲሱ የትምህርት ፋይናንስ ማዕቀፍ ከቤተሰብ ኢኮኖሚያዊ አቅም ውጪ በውጤት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንደሆነ ገልጸዋል።

ቀደም ሲል ተግባራዊ ተደርገው የነበሩት የዩኒቨርሲቲ በጀት አሰጣጥ ሥርዓቶችና የብድር ድብልቅ ሞዴሎች ተቋማቱንና ተማሪዎችን በቂ ድጋፍ ማድረግ ባለመቻላቸው መቋረጣቸውን ተናግረዋል።

አዲሱ ሥርዓት ወላጆች በፈቃደኝነት ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት የክፍያ ጫና እንዳይኖርባቸው የሚያደርግና ድህነት ትምህርት እንዳያስተጓጉል የሚያስችል ነው ተብሏል።

ለዚህም እንዲመች ፓርላማው የከፍተኛ ትምህርት ብድር ቦርድን ጨምሮ አስፈላጊውን የህግ ማሻሻያ በፍጥነት እንዲያጸድቅ ተጠይቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...