ወጣቶች ለአየር ንብረት ለውጥ የማትበገር አፍሪካን የሚገነቡ መሀንዲሶች ናቸው

Date:

ዛሬ ወጣቶቻችን የመጪው ዘመን የአየር ንብረት አጀንዳዎችን የሚቀርጹበትን “የአፍሪካ ወጣቶች የአየር ንብረት ጉባኤ 2025”ን በመዲናችን አዲስ አበባ በይፋ ከፍተናል።

አፍሪካ ለበካይ ጋዝ ልቀት ያላት አስተዋጽኦ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በድርቅ፣ በበረሃማነት፣ በምግብ ዋስትና ችግር፣ በጎርፍና በሌሎች አደጋዎች እየተፈተነች ትገኛለች።

አህጉራችን አፍሪካ ችግሮች ቢደራረቡባትም የተጨባጭ መፍትሔዎች አህጉር ስለመሆኗ የኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት ትግበራና ስኬት ሁነኛ ማሳያ ነው።

ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ኢኒሺየቲቭ በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 48 ቢሊዮን የሚጠጉ ችግኞችን ተክላለች፤ ለሚሊዮን ወጣቶቿ የሥራ ዕድል ፈጥራበታለች፤ የምግብ ዋስትናንም ማረጋገጥ ጀምራለች።

ሀገራችን ለቀጣናው ታዳሽና የንጹህ ኢነርጂ እያቀረበች መሆኗም አፍሪካ በሕዝቦቿ ንቁ ተሳትፎ ራዕይዋን እንደምታሳካ ተጨባጭ የተግባር ምሳሌ ነው።

ወጣቶች የአፍሪካ የጥንካሬና የተስፋ ምንጭ በመሆናቸው የማትበገር አፍሪካን ለመገንባት ፈጠራ መር መፍትሔዎችን በማፍለቅና በትብብር መሪ ሚናቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቅድመ-ክፍያ ውሎችን እንዳትፈጽም አገደ

የለንደን ፍርድ ቤት ደቡብ ሱዳን ከአሁን በኋላ አዳዲስ የነዳጅ...

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...