ዘመን ባንክ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ አገኝ

Date:

ዘመን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ10.2 ቢሊየን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ። የባንኩ ዓመታዊ የማኔጅመንት ስብሰባ ከሐምሌ 17 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን፣ በዕለቱም የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠን 116 ቢሊየን ብር መድረሱ ተገልጿል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይና የሪቴል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ አስራት ታደሰ ፣ ባለፈው በጀት ዓመት የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ከ14 ቢሊየን ብር በላይ፣ አጠቃላይ ገቢው 17.8 ቢሊየን ብር፣ እንዲሁም ጠቅላላ ካፒታሉ 26 ቢሊየን ብር መድረሱን አስታውቀዋል።

የባንኩ የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ32 በመቶ አድጎ 85.4 ቢሊየን ብር መድረሱም ተገልጿል።

በተጨማሪም የውጭ ምንዛሬ ግኝቱ 698 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ የተከማቸ የብድር መጠኑም 52.59 ቢሊየን ብር መድረሱ ከኦዲት በፊት በተደረጉ መረጃዎች ታውቋል።

ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በትምህርት ቤቶች የፋይናንስ እውቀት ማበልጸጊያ ስልጠናዎችን መስጠቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ ህብረተሰቡን ከፋይናንስ አጭበርባሪዎች ለመከላከል የተለያዩ ትምህርታዊ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...