የሄሊኮፕተር መከስከስ በሶማሊያ

Date:

የዩጋንዳ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር በሶማሊያ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ተከሰከሰች።
ሄሊኮፕተሯ ውስጥ ስምንት ሰዎች እንደነበሩም የሶማሊያ ዜና ምንጮች አስነብበዋል።

የአደጋው መጠን ምን ያህል ነው ስለሚለው ጉዳይም ዝርዝር ማብራሪያ እስካሁን አልወጣም።

ሄሊኮፕተሯ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ኤደን አዴ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ላይ ነው የተከሰከሰችው።

ከአውሮፕላን ማረፊያው የሚወጣ ከባድ ጭስ በአካባቢው መታየቱንም የዓይን እማኞች አረጋግጠዋል፡፡

ፍንዳታ ከሰማን በኋላ በሄሊኮፕተሯ ላይ እሳት እና ጭስ ተመልክተናል በሚል የአየር መንገዱ ሰራተኛ ፋራህ አብዱሌ አሳውቋል፡፡

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ለሄሊኮፕተሯ መከስከስ ምክንያቱ ምን እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም፡፡

ሄሊኮፕተሯ የዩጋንዳ ጦር ሀብት ስትሆን በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሚንቀሳቀሰው የሰላም አስከባሪ ሀይል አካል መሆኗም ተወስቷል።

የሶማሊያ መንግስት ከአል-ቃይዳ ጋር ትስስር አለው ከሚባለው አል -ሸባብ ጋር የሚያደርገውን ውጊያ ለማገዝ የገባ  ሀይል እንደሆነም ይታወቃል።

ዜናው እስከተጣናቀረበት ሰዓት ድረስ የስምንቱ ሰዎች እጣ ፈንታ ምንድን ነው የሚለውን የሶማሊያ መንግስት አላሳወቀም።

በሌላ በኩል የዩጋንዳ ጦር ሄሊኮፕተሯ የእኔ ናት ሲል ማረጋገጫ ሰቷል።

ዘገባው የቢቢሲና ሮይተርስ ነው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...