በትግራይ ክልል ከሁለት ዓመት በላይ የፈጀው ጦርነት በፕሪቶሪያ ስምምነት መቋጨቱን ተከትሎ፤ በክልሉ አሁን ላይ በሚጠበቀው ልክ ሰላም፣ መረጋጋት እና የዜጎች የመብት ተጠቃሚነት ተፈጥሯል ወይ?፣
በቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተተኩት ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ በክልሉ ለተከማቹት ችግሮች ምላሽ ይሰጣሉ ወይ?
ከዚህስ በሗላ በክልሉ የሚከናወነው ነገር ምን ይሆናል? በሚሉ ጉዳዮች ላይ በሀገራዊ ደረጃ በፓርቲነት ተመዝግበው በክልሉ በቀጥታ ከሚንቀሳቀሱ ከባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ክብሮም ተክላይ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የትግራይ ወኪል አቶ ይሳቅ ወልዳይ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል፡፡
በተጨማሪም የህወሓት አመራሮች ክፍፍል የትግራይን ሕዝብ ዋጋ እያስከፈለው ያለው ዋጋ እንዴት ይገለጻል? ከዚህ ነገርስ መውጫው ምን ይሆናል? ከሁለት ዓመት አንጻራዊ ሰላም በሗላ ዳግም ወደጦርነት ለመግባት ጫፍ ላይ ደርሷል ወይ? የሚሉ ሃሳቦችን በስፋት አንስተናል፡፡
ቆይታችንን እንድትከታለሉ በአክብሮት ጋበዝናችሁ!
ቆይታውን ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉https://youtu.be/-leLXwpDJxQ?si=SWQYoqS9dtZ9lwPn
