የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ቡድን በኢራን ያለው ሁኔታ እየተባባሰ ነው አለ

Date:

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ሰሞኑን ባወጣው መረጃ ጥቃቶች በመላው ኢራን እየተፈጸሙ በመሆናቸው ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን አስታወቀ።

እአአ ከመጋቢት 17 እስከ ሚያዚያ 3 ባለው ጊዜ ውስጥ በአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ሆስፒታሎች፣ የመኖሪያ አካባቢዎች፣ ገበያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የኢንዱስትሪ መንደሮች እና የባህል ቅርስ ስፍራዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ሲል ቡድኑ ገልጿል።

ኦቻ ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ መጋቢት 30 ድረስ ከ2,100 በላይ ንፁሀን ዜጎች መገደላቸውን፣ ከ27,900 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን እንዲሁም ከ 3.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ጦርነቱ እንደጎዳቸው አስታውቋል።

እናም ከጦርነቱ መጀመሪያ የካቲት 21 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት አምስት ሳምንታት ከ115,000 በላይ የሰላማዊ ሰዎች መገልገያዎች ተጎድተዋል ሲል አክሎ ተናግሯል።

ኦቻ በተጨማሪም “ወሳኝ በሆኑ የመሠረተ ልማት አውታሮች እና የኢንዱስትሪ መንደሮች ላይ የተካሄደው ጥቃት የመብራት፣ የውሃ እና የቴሌኮሙኒኬሽንን ጨምሮ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በማስተጓጎሉ ፈጣን እና ረዥም ጊዜ የሚቆይ የአካባቢ እና የጤና አደጋዎችን አስከትሏል” ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...