የቀድሞ ተጫዋችና የእግር ኳሱ አክቲቪስት የአድማስ ሎተሪ አሸናፊ ሆነ

Date:

“ሁሉን ያደረገው የ40 ሠልጣኝ ታዳጊዎችና የወላጆቻቸው ፀሎት ነው”
ሸዋረጋ ደስታ (የቀድሞ ተጫዋች)

በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

“አንድ ድምጿ ደስ የሚል እንስት ወደ እጄ ስልክ ደውላ አቶ ሸዋረጋ ደስታ ነዎት? ስትለኝ አዎን ነኝ ማን ልበል?አልኳት ወዲያውኑ ከአፌ ላይ ነጥቃ መጣደፍፍ በሚመስል አንደበት ከብሄራዊ ሎተሪ ነው የምደውለው አቶ ሸዋረጋ ደስታ እንኳን ደስ አልዎት፤የአድማስ ሎተሪ የአራተኛ ዕጣ አሸናፊ ሆነዋል ስትለኝ የሠማሁበትን ጆሮ በመጠራጠርና ወቅቱም የአፕሪል ዘ ፉል ቀን ስለሆነ ምን አልሽኝ ብዬ ስጠይቃት በደስታ በሚፈለቀለቅ ስሜት ውስጥ ሆና አቶ ሸዋረጋ ደስታ እንኳን ደስ አልዎት፤የአድማስ ሎተሪ የአራተኛ ዕጣ የ700ሺ ብር አሸናፊ ሆነዋል ብላ ስትደግምልኝ የኔ እመቤት ማነሽ?በዚህ ሠዓት የምን ቀልድ ነው የምትቀልጂው ብዬ ስልኩን ልዘጋባት ስል አቶ ሸዋረጋ ይሄ ቀልድ አይደለም ከብሄራዊ ሎተሪ ነው የምደውልሎት ለማረጋገጥ ከፈለጉ ዌብሳይታችን(ድረ-ገፃችን) ላይ ገብተው ማየት ይችላሉ ስትለኝ ቻው ሳልላትና ሳላስጨርሳት ወደ ዌብሳይቱ(ድረ-ገፁ)ዘው ብዬ ስገባ ስሜንና ብሩ ተደርድረው ሳይ ምክንያቱን በማላውቀው ሁኔታ በጣም ደነገጥኩ፤ወዲያውኑ የ40 ልጆቼ አምላክ ያደረገው ነው ብዬ ወደላይ አንጋጥቼ ይሄ እንዲሆን የፈቀደውን አምላኬን አመሠገንኩ”

ይህን ከላይ ያለውን ቃል ከ700ሺ ብር የአድማስ ሎተሪ አሸናፊነቱን በማረጋገጡ በማያባራ የደስታና የድንጋጤ ስሜት ውስጥ ሆኖ በተለይ ለሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል የተናገረው በሚሠጣቸው ድፍረት የተሞሉ አስተያየቶቹና ለእግር ኳሱ በሚያደርገው ትግል የእግር ኳሱ አክቲቪስት በሚል ስያሜ የሚጠራው ሸዋረጋ ደስታ ነው።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫዋችና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፣የቀድሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቤሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አባል፣የተጫዋቾችና የደጋፊዎች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የሆነው ሸዋረጋ ደስታ የአድማስ ሎተሪ የአራተኛ ዕጣ የ700ሺ ብር አሸናፊ መሆኑ ተረጋግጧል።

በርካታ የቀድሞ ተጫዋቾችንና አሠልጣኞችን እንዲሁም ለተቸገሩ ሠዎች የደግነት እጁን ፈጥኖ በመዘርጋት ተለይቶ የሚታወቀው፣ከ40 በላይ ታዳጊዎችን አሠባስቦ ከኪሱ ገንዘብ መድቦ የነገ የእግር ኳሱን ኮከቦች ለማፍራት ደፋ ቀና የሚለው ሸዋረጋ ደስታ ዕድል ወደቤቱ ሠተት ብላ በመምጣት የ700ሺ ብር የአድማስ ሎተሪ አሸናፊ አድርጋዋለች።

ካለፉት ሶስት ዓመታት ጀምሮ የባንክ የታዳጊዎች የእግር ኳስ ማሠልጠኛ ፕሮጀክት ቶሎሳ ሠፈር ፕሮጀክትን በማቋቋም የነገ ሀገር ተረካቢ ታዳጊዎችን ያለምንም ክፍያ ከኪሱ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት 40 ታዳጊውች በነፃ ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ላይ የሚገኘው ሸዋረጋ ደስታ የ700ሺ ብር አሸናፊ በመሆኑ ምን አይነት ስሜት እንደተፈጠረ በስልክ ጠይቀነው”ይሄ ሁሉ የ40ዎቹ ልጆቼ(ሠልጣኞች) አምላክ ስራ ነው፤ይሄ እንዲሆን የፈቀደው አምላኬ ነው በልጆቼ ስም ዝቅ ብዬ አመሠግናለሁ”ካለ በኃላ”ላለፉት ሶስት አመታት ማንም ሳይደግፈኝ ከኪሴ በማውጣት ለ40 ታዳጊዎች ማልያ፣ኳስ በመግዛትና የሜዳ ጭምር በመክፈል ብዙ ዋጋ ከፍያለሁ፤የልጆቼ አምላክ የከፈልኩትን ዋጋ በማየት እንዲሁም ለታዳጊዎቹ የተሻለ ነገር እንዳደርግ የአድማስ ሎተሪ አሸናፊ አድርጎኛል፤ሁሉን ያደረገው የ40 ሠልጣኝ ታዳጊዎችና የወላጆቻቸው ፀሎት ነው፤ሁሌም በጎ ነገር ስራ አምላክ ባላሠብከው መንገድ ይከፍልሀል”ብሏል።

ያገኘኸውን ገንዘብ ምን ልታደርግበት ነው ያሠብከው?በሚል በመጨረሻ ለቀረበለት ጥያቄ”ይሄ እንዲሆን የፈቀደው የልጆቼ አምላክ ነው፤40ዎቹ ሠልጣኞችን በተሻለ ለማሠልጠን እንዲሁም ልጆቼን ስውዲን ላይ ለሚካሄደው የጎትዬ ካፕ እንዲሳተፉ የተለያየ ጥረት እያደረኩ ነው፤ፈጣሪ ፈቅዶ ከተሳካልኝ ለጉዞአችን አውለዋለሁ”ካለ በኃላ የአድማስ ሎተሪ አሸናፊ መሆኔ ከተሠማ በኋላ የእንኳን ደስ አለህ ስሜታቸውን የገለፁልኝ ገና ለገና ሎተሪ ደርሶታል ብለው፣ለልጆቼ እንደሚውል ሳይረዱ የብድር ማመልከቻ ያስገቡትን በሙሉ ከልብ አመሠግናለሁ”ሲል አስተያየቱን አጠናቋል የ700ሺ ብር የኘድማስ ሎተሪው አሸናፊ ሸዋረጋ ደስታ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሕገ መንግሥቱ መገንጠልን ይፈቅዳል ፤ ሕዝቡ ደግሞ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ዋጋ ይከፍላል”

አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል(የ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች›› መጽሐፍ ደራሲ) ግዮን መጽሔት :-...

ባለሙያ ባልሆኑ ግለሰቦች የሚሰራጭ የተዛባ መረጃ በታካሚዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነዉ

የሳይካትሪስት የሙያ ፈቃድና ሥልጠና የሌላቸው ግለሰቦች በተለያዩ መገናኛ...

የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የ1.2 ቢሊዮን ዩሮ ስምምነት ሊፈራረሙ ነው

በአውሮፓ ህብረት እና በኢትዮጵያ መካከል በሚካሄደው የንግድ ፎረም መክፈቻ...

የአዳዲስ እና የሁለተኛ ዙር መራጮች አቅምና ሚና

ግዮን መጽሔት :- በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ የአዳዲስ (ለመጀመሪያ...