የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም…

Date:

ማንኮራፋት/Snoring/ በእንቅልፍ ወቅት በአፍ እና በአፍንጫ ውስጥ ያለው የአየር ፍሰት በከፊል ሲዘጋ ይከሰታል፡፡ ይህም በጉሮሮ ውስጥ ያሉት ሕብረ ሕዋሳት እንዲርገበገቡ እና ከፍተኛ ድምፅ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

ማንኮራፋት ከአጠገባቸው/ከጉናቸው በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮአዊ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ከፍተኛ ድምጽ ያለው ማንኮራፋት ኦብስትራክቲቭ ስሊፕ አፕኒያ ከሚባል የጤና ችግር ጋር ይያያዛል። ይህ የጤና ችግር የጉሮሮ ክፍል ግድግዳዎች እንዲፍታታ እና እንዲጠብ በማድረግ የተለመደ የመተንፈስ ሥርዓትን በማስተጓጎል የኦክስጅን እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል።

ኦብስትራክቲቭ ስሊፕ አፕኒያ የልብ የሥራ ማቆም ዕድልን በ140 ፐርሰንት ፣ በስትሮክ የመመታት ዕድልን 60 በመቶ እንዲሁም ለልብ ህመም የመጋለጥ ዕድልን 30 በመቶ እንደሚጨምር ጥናቶች ያመለክታሉ። በትዳር ውስጥ ያሉ ጥንዶችም በማንኮራፋት ምክንያት ክፍል ለይተው እስከመተኛት ሊደርሱ ይችላሉ።

ማንኮራፋትን ወይም ስሊፕ አፕኒያን ለማስቀረት ከሚረዱ አማራጮች መካከል  ክብደት/ውፍረትን መቀነስ ፣ ሲጋራ ማጨስን ማቆም ፣ የአልኮል መጠን መቀነስ ፣ አተኛኘት እና ትራስ አጠቃቀምን ማስተካከል መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህን አድርጎ ለውጥ ካልመጣ ግን ወደ ጤና ተቋማት ሔዶ ተገቢውን ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...