የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት ጤና አባልነት ፕሮግራምን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።
አባል በመሆንዎ የኩላሊት በሽታን ለመከላከል፣ የኩላሊት ጤና ግንዛቤን ለማሳደግ እና የኩላሊት ህክምና አገልግሎቶች ተደራሽነትን ለማስፋፋት በሚደረገው ሀገራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ ይሆናሉ።
እያንዳንዱ አባልነት ለአንድ ሰው ተስፋ፣ ለአንድ ቤተሰብ ድጋፍ እና ለጤናማ ኢትዮጵያ መሠረት ይሆናል።
የአባልነት ጥቅሞች
የግለሰብ አባላት፦ 100% ነፃ የኩላሊት እጥበት (ዳያሊሲስ) አገልግሎት
የቤተሰብ አባላት፦ 75% ቅናሽ የኩላሊት እጥበት (ዳያሊሲስ) አገልግሎት
የማኅበረሰብ ድጋፍ ተጠቃሚዎች፦ 75% ቅናሽ የኩላሊት እጥበት (ዳያሊሲስ) አገልግሎት
የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ተጠቃሚዎች፦ 100% ነፃ የኩላሊት እጥበት (ዳያሊሲስ) አገልግሎት
የአባልነት ሰርተፍኬት፦ የአባልነት ሰርተፍኬት ይሰጥዎታል።
ዛሬውኑ አባል ይሁኑ፤ ህይወትን በማዳን የለውጡ አካል ይሁኑ!
ለበለጠ መረጃ፦
+251 97 933 3322 / +251 99 353 3772
#ሜሪጆይኢትዮጵያ#የኩላሊትጤና#አባልነት#ህይወትንእናድን
