የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በጋምቤላ የተጠለሉ ስደተኞችላይ የሚሰራጩ “የተሳሳቱ መረጃዎች” በእጅጉ እንዳሳሰቡት አስታወቀ

Date:

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR)፤ በጋምቤላ ክልል የተጠለሉ ስደተኞች ላይ በማነጣጠር በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ “የተሳሳቱ መረጃዎች” “በእጅጉ እንዳሳሰቡት” ገለጸ።

ለሁኔታው በአፋጣኝ መፍትሔ ካልተበጀለት በአካባቢው ውጥረትን ሊያባብስ እንደሚችል ድርጅቱ አስጠንቅቋል።

የተመድ የስደተኞች መርጃ ተቋሙ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው፤ ማክሰኞ ታህሳስ 14 ቀን  2018 ባወጣው መግለጫ ነው።

ድርጅቱ በዚሁ መግለጫው፤ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በሀገራቸው ከሚደርስባቸው ጥቃት “ደህንነትንና ጥበቃን ለማግኘት” እንደሆነ አስታውሷል።

የጥገኝነት ሲቪልና ሰብአዊ ባህሪያት “ለድርድር የማይቀርብ መርህ” መሆኑን በመግለጫው አጽንኦት የሰጠው ድርጅቱ፤ “በትጥቅ እንቅስቃሴ” ውስጥ ሲሳተፍ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ በሀገሩ ሕግ መሰረት ተጠያቂ እንደሚሆን አመልክቷል።

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩ መረጃዎች፤ ከደቡብ ሱዳን ተፈናቅለው በጋምቤላ ክልል ተጠልለው የሚገኙ ስደተኞች በክልሉ ሰሞኑን በተቀሰቀሰው ግጭት ውስጥ ተሳትፎ እንዳላቸው ወንጅለው ነበር።

ድርጅቱ  በመግለጫው ስደተኞች ላይ ያነጣጠሩ “የተሳሰቱ መረጃዎች” መሰራጨታቸውን ቢገልጽም፤ ስለ መረጃዎቹ ምንነት በግልጽ ያለው ነገር የለም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...