የግብርና ሚኒስቴር የቡና ላኪዎች የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት የሚጠይቀውን ዝቅተኛ የመነሻ ካፒታል በግለሰብ ደረጃ በ900 በመቶ እንዲሁም ለአክሲዮን ማህበራትና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበራት ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ጭማሪ የተደረገበትን ረቂቅ መመሪያ አዉጥቷል።
በዚሁ ረቂቅ መሰረት፣ የግል የቡና ላኪዎች ከዚህ ቀደም ይጠበቅባቸው የነበረው አንድ ሚሊዮን ብር ዝቅተኛ ካፒታል ወደ 10 ሚሊዮን ብር እንዲያድግ ታቅዷል። በተጨማሪም፣ አመልካቾች የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴን የሚያሳይ በባንክ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ለአክሲዮን ማህበራት እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበራት የሚፈለገው ዝቅተኛ የመነሻ ካፒታል ከ 1 ሚሊዮን 500 መቶ ሺህ ብር ወደ 15 ሚሊዮን ብር ከፍ እንዲል የቀረበ ሲሆን፣ ከማህበሩ መስራቾች መካከል ቢያንስ ሁለቱ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አባላት የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴ የሚያሳይ የባንክ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይላል።
CapitalNews
