ኢትዮጵያ ከስንዴ ተረጂነት ወጥታ ምርቱን በስፋት በማምረት ከአገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለውጭ ገበያ እያቀረበች እንደምትገኝ የሚታወቅ ሲሆን፤ ፓርቲው የዘንድሮውን ምርጫ መወዳደሪያ ምልክት የስንዴ ነዶ ማድረጉንም በይፋ አብስሯል።
የስንዴ ነዶ ከምርታማነት ባለፈ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን የሚያሳይ የጥንካሬ ምልክት መሆኑም ተገልጿል። ስንዴ የዓለምን የምግብ ልዕልና የሚያረጋግጥ መሆኑን የገለጸው ፓርቲው፣ የምርጫ ምልክቱም ይኸው የስንዴ ነዶ መሆኑን በይፋ አረጋግጧል።
በሌላ በኩል የፓርቲው ማኒፌስቶ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት አገር” በሚል መሪ ቃል የቀረበ ሲሆን፤ ሰነዱ በ169 ገጾች ተቀንብቦ የቀረቡ 15 ዋና ዋና ይዘቶችን አካቷል።
በማኒፌስቶው ውስጥ ከተካተቱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፦ ‘ትላንትን ማከም ነገን መተለም’፣ ፍትሐዊት ኢትዮጵያ፣ ከዕዳ ወደ ምንዳ የተሸጋገረ ኢኮኖሚ፣ ከውሃ እስከ ውሃ፣ ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ማስፈን፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እና ጸጋን ወደ ሀብት መቀየር የሚሉ ሐሳቦች ይገኙበታል።
በተጨማሪም ኢንዱስትሪን ማስፋፋት፣ ኢትዮጵያውያንን በመሠረተ ልማት ማስተሳሰር፣ አገር የሚያበለጽግ ጤናማ ዜጋ ማፍራት፣ አካታችነት፣ ከተሞችን የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ እና ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍ ማድረግ በማኒፌስቶው የተገለጹ ቁልፍ ነጥቦች ናቸው።
