ቭላድሚር ፓድሪኖ ሎፔዝ በቪዲዮ ባስተላላፉት መልዕክት፤ ቬንዚዌላ አይታ የማታውቀው “አስከፊ ጥቃት” ገጥሟታል፤ በ“ማዱሮ ትዕዛዝ” የጦር ኃይሉ በመላ አገሪቱ ይሰማራል ብለዋል።
“አጥቅተውናል ነገር ግን እንድንበረከክ ግን አያደርጉንም” ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ ጨምረው ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በቬንዚዌላ ወታደራዊ የጦር ካምፖች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውንና የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ከእነባለቤታቸው በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ፤ ማዱሮና ባለቤታቸው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከአገር አንዲወጡ ተደርገዋል ብለዋል።
አሜሪካ ኒኮላስ ማዱሮ ዓለም አቀፍ አደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪ ድርጅትን ይመራሉ የሚል ክስ ለረጅም ጊዜ ስታቀርብ ቆይታለች። ዋሽንግተን ፕሬዝዳንቱን በቁጥጥር ስር ማዋል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጡ ሰዎች የ50 ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ አውጥታ እንደነበር ቢቢሲ አስታውሷል፡፡
