የተለያዩ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች በሀገር ውስጥ ምርት እየተካሁ ነው

Date:

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ የኮንስትራክሽን ግብዓት ልማት አቅርቦት ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጠንክር መኩሪያ ከኤፍ ኤም 97.1 ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከውጭ የሚገቡ የኮንትራክሽን ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን 80 በመቶ በሀገር ውስጥ ለመተካት  የ10 ዓመት እቅድ አቅዶ እየሰራ እንደሆነም አቶ ጠንክር መኩሪያ ተናግረዋል፡፡ በ2017ዓ.ም እቅድ መሰረት 45 በመቶ የነበረው የሀገር ውስጥ የኮንስትራክሽን ግብዓት ምርት ከ8 በመቶ በላይ አድጎ 53 በመቶ መድረሱንም ጠቅሰዋል፡፡

እንደ አቶ መኩሪያ ገለፃ የሲሚንቶ ምርት ፍላጎትን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈን የተቻለ ሲሆን ማርብል እና ግራናይትም 70 በመቶው በሀገር ውስጥ እየተመረተ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የሌሎች የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን አቅርቦት ለማሳደግም በዘላቂነት መስራት እንደሚደባ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ የኮንስትራክሽን ግብዓት ልማት አቅርቦት ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጠንክር መኩሪያ ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከጂሃድና ከእምቢተኝነት ውጭ ሌላ መንገድ የለም!

የኢራኑ ከፍተኛ መሪ ሞጅተባ ኻመነኢ እሁድ ዕለት በቴሌግራም ገጻቸው...

አሜሪካ እና ኢራን ዳግም ወደ ድርድር ?

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር ሙሉ በሙሉ እንዳልወጣች፣ ነገር...

እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት የሐማስ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን መገደሉ ተዘገበ

እስራኤል እሁድ ዕለት በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት በሐማስ የሚመራው የፍልስጤም...

አሰቃቂውን ጥቃት የፈጸሙ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ ፓትርያርኩ ጠየቁ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት...