የሀገር ውስጥ የመድሃኒት ምርት የገበያ ድርሻ ወደ 41 በመቶ አደገ

Date:

በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የመድሃኒት ምርት የገበያ ድርሻ ከ8 በመቶ ወደ 41 በመቶ ማደጉን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ አስታወቁ።

ይህ ጭማሪ የመጣው የሀገር ውስጥ የመድሃኒት አምራቾች ምርቶች በግዥ ሂደት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው በመደረጉ እንደሆነ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን እድገት ቢታይም፣ ለመድሃኒት ምርት የሚያገለግሉ አብዛኛዎቹ ጥሬ እቃዎች አሁንም ከውጭ የሚገቡ መሆናቸውን ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቁመዋል። ይህንን ለመቀየር በሀገር ውስጥ የሚገኙ ጥሬ እቃዎች ጥቅም ላይ መዋል እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በበኩሉ፣ የካሳቫ ስታርች ምርት ለፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪዎች ያለውን አዋጭነት የሚያሳይ ጥናት ማድረጉን ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከጂሃድና ከእምቢተኝነት ውጭ ሌላ መንገድ የለም!

የኢራኑ ከፍተኛ መሪ ሞጅተባ ኻመነኢ እሁድ ዕለት በቴሌግራም ገጻቸው...

አሜሪካ እና ኢራን ዳግም ወደ ድርድር ?

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር ሙሉ በሙሉ እንዳልወጣች፣ ነገር...

እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት የሐማስ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን መገደሉ ተዘገበ

እስራኤል እሁድ ዕለት በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት በሐማስ የሚመራው የፍልስጤም...

አሰቃቂውን ጥቃት የፈጸሙ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ ፓትርያርኩ ጠየቁ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት...