የትወናና የሞዴሊንግ ምልመላ ወኪል(ካስቲንግ ኤጀንት) የሚያስተዋውቅ እንዲሁም የተደበቀን ተሰጥኦን ገሀድ ለማዉጣት የጎላ አስተዋፅኦ እንዳለው የተነገረለት ቲ ካስቲንግ ኤጀንሲ ዌብሳይትናና አፕሊኬሽን በይፋ ሥራ ጀመረ፡፡
በሀገራችን እንዲሁም በዉጭ ሀገራትና ከተለያዩ የቴሌቪዥን ፕሮዳክሽን ስራዎች ጋር በትብብር በመስራት በሚታወቀው “ቴዲ ሾዉ መልቲ ሚዲያ” አማካኝነት በከፍተኛ ጥናት የበለፀገዉ ዌብሳይትና አፕሊኬሽን፣ “ቲ_ካስቲንግ ኤጀንሲ!” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን በሀገራችንም የመጀመሪያው የዲጂታል የታለንትና ተሰጥኦ ምልመላ ወኪል እንደሆነም ተነግሯል።
የቲ-ካስቲንግ ኤጀንሲ ሃላፊዎች እንዳብራሩት፤”በአገራችን ብቻ ሳይሆን በውጪ አገር ታላላቅ ፕሮዳክሽን ካምፓኒዎች መተወን ለሚፈልጉ፣ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ስራ፣ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች፣ የሲኒማ ፊልሞች ፣ የሙዚቃ ክሊፖች ላይ የትወና ስራ ያመቻቻል፡፡
እንዲሁም ብራንድ አምባሳደርነት ሙያን ከፈላጊ ድርጅቶች ጋር ለማገናኘት ምቹና ቀጥታ አመቺ ሁኔታ የሚፈጥር ዘመናዊ የዲጂታል ፕላትፎርም ነው፡፡
