የቴሌብር ጥምረት ከሱዳንና ጅቡቲ ጋር!

Date:

ኢትዮ ቴሌኮም ከሱዳንና ጅቡቲ ጋር ክልላዊ የክፍያ ትስስር ለመፍጠር እያካሄድው ያለው ድርድር፣ ኢትዮጵያ የቀጣናው ቁልፍ ተዋናይና በምሥራቅ አፍሪካ እንዲሁም በአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ውህደት ጉልህ ሚና መጫወት እንደምትችል የሚያሳይ መሆኑን የስፑትኒክ ትንተና ይጠቁማል፡፡

የክፍያ ስርዓቱ ለሀገራቱ ምን ይፈይዳል? ቁልፍ ዝርዝር ጉዳዮች፦

*ቀልጣፋ ግብይት፦ ትስስሩ በሀገራቱ መካከል የሚደረገውን ግብይት እስከ እጅ ስልክዎ ያሳጥራል፣

*ተመጣጣኝ የአገልግሎት ክፍያ፦ በዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የሚፈጸሙ ግብይቶችን ያርቃል፣

*በራስ ገንዘብ መገበያየት፦ ቴሌብርን ከፓን አፍሪካ የግብይትና ክፍያ ስርዓት ጋር በማዋሃድ የሚቀርበው አገልግሎቱ፤ በሀገራቱ መካከል የሚደረገውን ግብይት ከዶላር ጥገኝነት ነፃ ሊያወጣ እንደሚችል ትንተናው ያመለክታል፡፡

ለምን ሱዳንና ጁቡቲ?

የሱዳን የዲጂታል የክፍያ ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎት የሚሰጡ በመሆኑ ከቴሌብር ጋር የሚኖረውን ጥምረት ያቀለዋል። ከኢትዮጵያ የገቢ ወጪ መስመር ጅቡቲ ጋር ኢኮኖሚያዊ ትስስርም ይበልጥ ይጠነክራል።

ኢትዮ ቲሌኮም በበጀት ዓመቱ በቴሌብር 2.38 ትሪሊየን ብር የተዘዋወረ ሲሆን፤ አገልግሎቱ ከተጀመረ ጀምሮ በኢኮኖሚው ውስጥ 4.93 ትሪሊየን ብር ማዘዋወር እንደቻለ ስፑትኒክ አስታውሷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...