የትግራይ ክልል ነዋሪዎች በፍርሃት ስደት እያሰቡ ነው ተባለ

Date:

የትግራይ ክልል ነዋሪዎች በፍርሀት ክልሉን ለቀው ለመሸሽ እያሰቡ መሆኑን ኤኤፍፒ ዘግቧል


በአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደርና ህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መካከል የተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ ወደ ውጥረት መሻገሩን የጠቀሰው ዘገባው አንደኛው አንጃ በመቀሌ የሚገኘውን ማዘጋጃ ቤት መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡

አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር ለዜና አውታሩ ሲናገር ‹‹አሁን ህዝቡ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ካለፈው የከፋ ሁኔታ ሊያጋጥም ይችላል በሚል ስጋት ላይ ነው›› ብሏል፡፡ ሌላ ነዋሪ ደግሞ ህዝቡ ክልሉን ጥሎ ለመሸሽ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ገልፃለች፡፡ ምህረት የተባለችው ይህች የ27 አመት ወጣት ስትናገር ‹‹ባለፈው ጦርነት ጊዜ በመቀሌ ውስጥ ታሽገን ነበር፡፡ አሁን ያ እንዲደገም አንፈልግም፡፡›› ብላለች፡፡

ጨምራም ‹‹አሁን ክልሉን ለቀን ለመውጣት ጥረት እያደረግን ነው፡፡ ነገር ግን የአውሮፕላን ትኬት ለመቁረጥ ስንፈልግ ሰሞኑን ያሉት በረራዎች የሞሉ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡ ስለዚህም ክልሉን ለመልቀቅ ሌሎች አማራጮችን እየፈለግን ነው›› በማለት አስረድታ ነዋሪው በፍርሀት ውስጥ እንደሚገኝ ገልፃለች፡፡

እንደኤኤፍፒ ዘገባ የደብረፅዮን አንጃ የመቀሌ ከተማን ማዘጋጃ ቤት ትላንት የተቆጣጠረ ሲሆን የራሱን ከንቲባም ሾሟል፡፡ እንዲሁም በመቀሌ የሚገኘውን የኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ በቁጥጥሩ ስር አስገብቷል፡፡ የዶክተር ደብረፅዮን ቃል አቀባይ ለዜና አውታሩ ሲናገሩ ‹‹ቀደም ሲል ተመርጠው የነበሩት ከንቲባ በአቶ ጌታቸው ረዳ ተባረው ነበር፡፡ ያ ደግሞ ህጋዊ አልነበረም፡፡ ስለዚህም አሁን እኚያን ከንቲባ መልሰን ሾመናቸዋል›› ብለዋል፡ይሁንና በመቀሌ ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሰው ዘገባው አቶ ሀጎስ የተባሉ የከተማው ነዋሪ የሰጡትን አስተያየት አቅርቧል፡፡ አቶ ሀጎስ በአሁኑ ወቅት የከተማው ነዋሪ ያለውን ገንዘብ ለማውጣት ባንክ ቤት በር ላይ ተሰልፎ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ ይህም የሆነው ፖለቲካዊ ውጥረቱን ተከትሎ የመሰረታዊ አገልግሎት መቋረጥ ሊከሰት ይችላል በሚል መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሀጎስ ‹‹ነዋሪው ሌላ ጦርነትን አይደግፍም፡፡ ሰልችቶታል›› ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!! በክርስቲያኖች ዘንድ ጥምቀት...

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...

በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ...

ንግድ ባንክ “ስታርፔይ” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ሥርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ...