የአዲስ አበባ ታክሲዎች ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ክፍያ እንዲሰበስቡ ተወሰነ

Date:

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የታክሲ አሽከርካሪዎች ከተወሰነው ታሪፍ በላይ እንዲሚያስከፍሉ ከማኅበረሰቡ የሚነሳውን ቅሬታ ለመፍታት ክፍያው ከመነሻው እንዲሰበሰብ የሚያስገድድ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስታውቋል።

አሽከርካሪዎች በታሪፍ መመሪያው መሠረት ብቻ ከመነሻው የትራንስፖርት ክፍያ እንዲሰበስቡ ለማስቻል ተቆጣጣሪዎች በመነሻ መጫኛ ቦታዎች ላይ ተመድበው ሥራ መጀመራቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ተናግረዋል።

ይህ አሠራር በጉዞ ወቅት “ሒሳብ ጨምሩ” በሚል ከአሽከርካሪዎች የሚነሳውን አግባብነት የሌለው ጥያቄ ለመግታት የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

ይሁን እንጂ አዲሱ አሠራር ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ አንዳንድ ተግዳሮቶች መፈጠራቸውን የቢሮው ኃላፊዎች ጠቁመዋል።

በከተማዋ በሚገኙ መነሻዎች ላይ ክፍያውን አስቀድሞ በመሰብሰብ ሂደት የተወሰነ ጊዜ እየወሰደ መሆኑ በማኅበረሰቡ በኩል ቅሬታ መፍጠሩ ተገልጿል።

በተመሳሳይ አንዳንድ አሽከርካሪዎች መንገድ ከጀመሩ በኋላ ታሪፍ የመጨመር አዝማሚያዎችን እያሳዩ መሆናቸውን ቢሮው አስታውቋል።

ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ማኅበረሰቡ የጉዳዩን ፋይዳ በመገንዘብ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግና ህገ-ወጥ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ጥቆማዎችን በመስጠት የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አቶ ዳኛቸው አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ያለ ረዳት በሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ሲገለጽ መቆየቱ የሚታወስ ቢሆንም፤ ቢሮው በአሁኑ ወቅት ትኩረቱን አዲሱ የአሠራር ሥርዓት ላይ ማድረጉን አመልክቷል።

ይሁን እንጂ የረዳት አጠቃቀምን በተመለከተ ግልጽና ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት እንደሚያስፈልግ አቶ ዳኛቸው ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...