የምላስ ነጭ መሆን መንስኤው ካንዲዳ ከሚባሉ ዩስት ሲሆን የምላስ መንጣት ደግሞ ካንዲዲያሲስ ይባላል፡፡ ካንዲዳ ለሰውነታችን እጅግ ጠቃሚ ናቸው ነገር ግን ከመጠን በላይ በሚያድጉበት ወቅት ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራሉ።
መንስኤዎቹን፡-
• የበሽታ የመከላከል አቅም መዳከም
• ለረጅም ጊዜ አንቲባዮቲክ መድሀኒቶች መጠቀም
• የወሊድ መቆጣጠሪያ መውሰድ
• ኢንሱሊን (የስኳር በሽታ መድሀኒት)
• እርግዝና መኖር
• ደካማ የአፍ ጤንነት አጠባበቅ
• የአፍ መድረቅ
• ትምባሆ መጠቀም
• አልኮል መጠቀም
• ጣፋጭ ምግቦችን መውሰድ
ምልክቶቹ፡-
• እንደ አይብ የመሰለ ነጭ ነገር ምላስ ላይ መታየት
• የምግብ ጣእም አለመለየት
• በእጅ በሚነኩበት ጊዜ መድማት
• በአፍ ዙሪያ መቅላት
• ለማኘክ ፣ለመዋጥ መቸገር
የቤት ውስጥ ህክምናዎች፡-
በደቃቅ ጨው ለአንድ ደቂቃ በጥርስ ብሩሽ ምላስን መቦረሽ፡፡ ከዚያም በሙቅ ውሀ በደንብ መታጠብ፡፡ ሁለት ጊዜ በየቀኑ ይድገሙ እና በሳምንት ውስጥ የሚፈልጉትን ውጤቶች ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም ለብ ያለ ውሀ ውስጥ 1 የሻይ ማንኪያ ጨው ይቀላቅሉ፡፡ በዚህ የጨው ውሀ አፍን በመሙላት ይጉመጥሞጡ። ሾርባ ላይ እሬት (አሎቬራ)በመጨመር በአፍ ውስጥ መጉመጥመጥ እንዲሁም 1 ማንኪያ የአሎቬራ ጭማቂ ይጠጡ ይህን መድሀኒት በየቀኑ ማድረግ ለ 2 ሳምንታት ያህል ማድረግ፡፡
የሚያጠቡ እናቶች ሊያሶግዷቸው የሚገቡ የምግብ ዓይነቶች
እናቶች በተለይም ከ6 ወር በታች ያሉ ጨቅላ ህጻናትን በሚያጠቡበት ወቅት ከምግብ አይነቶቻቸው ውስጥ ሊያሶግዷቸው ከሚገቡ የምግብ ዝርዝሮች ውስጥ ተከታዮቹ ነጥቦች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የስንዴ ምርቶችን፣ ቡና፣ ሻይ፣ አልኮል መጠጥ፣ የሾርባ ቅጠል፣ ጥሬ ወተት፣ ሎሚ፣ ብርቱካን፣ ኦቾሎኒ፣ ነጭ ሽንኩርት ይጠቀሳሉ፡፡
ኮልስተሮል ያለባቸዉ ሰዎች ማድረግ ያለባቸውና የሌለባቸው ነገሮች
ማድረግ ያለባቸዉ፡-
- በመጀመሪያ የኮሌስትሮል መጠጥንዎን ማወቅ በአመጋገብ ሰዓት የደም ኮሌስትሮልን መጠን ከፍ ሊያደርግ የሚችሉ ምግቦችን ማስወገድ፡፡
- በምግብዎ ውስጥ ያለውን ስብ መጠን ማወቅ በስብ የበለጸጉ ምግቦች ክብደትን እንዲጨምር አልያም ከፍ ወዳለ የደም ኮሌስትሮል ደረጃ ሊወስድ ይችላል።
- የወይራ ዘይት እና ከአትከልት የሚዘጋጁ ዘይቶች መጠቀም፡፡
- ፋይበርነት ያላቸው ምግቦች የደም ኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ ሊረዳሉ እሱም፡- ሩዝ ፣ ገብስ ፣ የደረቁ አተር እና ባቄላዎች፣ ፍራፍሬዎች ውስጥ እንደ ፖም ያሉ ፍራፍሬዎች መጠቀም፡፡
- በቀን ውስጥ ቢያንስ 30 ደቂቃ ያክል የሰውነት እንቅስቃሴ ማሠራት፤
- የታሸጉ ምግቦች ፣መጠጦች ማስወገድ፤
- ከመጠን በላይ ወፍራም ካለ ክብደት መቀነስ፤
ማድረግ የሌለባቸው፡-
- አለማጨስ፤
- ጨው አለመጠቀም፤
- እንደ አልሞንድ፣ ዎልት፣ ኦቾሎኒ አለመጠቀም፤
- ስብ አለመመገብ፤
የደረቀ ጸጉር ለማለስለስ የሚረዱ ዘዴዎች
- የኮኮናት ፣የጉሎ ወይም የወይራ ዘይት ፡-እነዚህን አፍልቶ ቆዳ ቆዳ በመቀባት በስሱ ማሳጅ ማድረግ ከዛም ከ30-45 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ፤
- እርጎ እና የወይራ ዘይት በመቀላቀል መቀባት ከዛም ከ15-20 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ፤
- ሙዝ በጁስ መልክ በማዘጋጀት የጉሎ ዘይት መቀላቀል ከዛም ለ1 ሰአት አቆይቶ መታጠብ፤
- 1 የሻይ ማንኪያ የአፕል አቼቶ ፣2 የሻይ ማንኪያ የወይራ ዘይት እና 3 ነጩን የእንቁላል ክፍል በመለየት ማዋሃድ ከዛም ከ20-30 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ፤
- 1 ሙዝ በጁስ መልክ በማዘጋጀት የጉሎ ዘይት መቀላቀል ከዛም ቆዳ ቆዳ እና ጸጉርን በደንብ አዳርሶ መቀባት እና ለ1 ሰአት ያክል አቆይቶ መታጠብ፤
