ተቋሙ በ2017 አ.ም ሰባት ወራት ውስጥ ብልሹ አስራርን ለማሶገድ ባከናወናቸው ተግባራት በ22 አመራርና ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቋል፡፡
እርምጃው የተወሰደው ከደንበኞች የቀረቡ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ እና አስፈላጊው ማጣሪያ ተደርጎ መሆኑን በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ መላኩ ታዬ ተናግረዋል፡፡ እርምጃ ከተወሰደባቸው አመራር እና ሰራተኞች መካከል 3ቱ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እና 19ኙ የደመወዝ ቅጣት የተቀጡ መሆናቸውን ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የብልሹ አሰራር እና የሙስና ጥቆማ መስጫ ዲጂታል የሞባይል መተግበሪያ ስራ ላይ ማዋሉ የሚታወስ ነው፡፡