
ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት ለስድሰት ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል የ240 ሚሊየን ዩሮ (የ32.3 ቢሊየን ብር) የልማት ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል ፡፡
የድጋፍ ስምምነቱ በዋናነት የስራ ዕድል የሚፈጥሩ የግብርና ስራዎችን፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በመጠቀም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ልማትን በማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት፣ የዴሞክራሲ ተቋማትን በማጠናከር በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን አስተዳደርና አካታችነትን በማሻሻል መረጋጋትን ለማስፈን የማያግዝ ነው ።
እንዲሁም በግጭት የተጉዱ የጤና ተቋማትን ወደ አገልግሎት ለመመለስና እንዲሁም ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል ፡፡
የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት ድጋፉ የግሉ ዘርፍን የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት በኢኮኖሚው ውስጥ እንዲጨምር ለማገዝ፣ የታክስና ጉምሩክ ስርዓቱን ለማዘመን፣ የግብርና፣ጤናና ትምህርት አገልግሎትን ለማሳደግ የሚያስችል ነው ፡፡