የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ (App) መተግበርያ ወደ ስራ ገባ

Date:

በባለፉት አስርት አመታት በልጆች ዙርያ የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ የቆየው የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ፤ 7 አመታቱን በሀገራችን የሙሉ ጊዜ የልጆች የቴሌቪዥን ጣቢያ በመጀመር ፈር ቀዳጅ ነዉ።

በተለይ በልጆችና ቤተሠቦቻቸው ዘንድ ሠፊ ተቀባይነት በማግኘት የትውልድ ግንባታ ላይ እየሠራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ ዓላማና ተደራሽነቱን ይበልጥ በማስፋት፤“ከመህቡብ ቴክኖሎጂስ” ጋር በመተባበር “የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ” (Ye Ethiopia Lijoch Supper App) በሚል መጠሪያ መልከ ብዙ ገፅታንና ይዘትን የተላበሰ   የሞባይል መተግበሪያ ሠርቶ ሐሙስ ሐምሌ 17- 2017 ዓ.ም . በስካይ ላይት ሆቴል አዲስ መተግበሪያ ( App) ጥሪ የተደረገችዉ እንግዶች በተገኙበት አስመርቋል ።

የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን ያስመረቀው ይህ መተግበርያ በውስጡ 10 የሚሆኑ ይዘቶች ተካተዉበታል።

ከነዚህ ውስጥ ሙዚቃዎች ፣ ጌሞች ፣ ፊልሞች ፣ተማሪ ቤት፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ ሥነ-ምግባር፣ የቋንቋ ማስተማሪያ ቪዲዮና ልጆችን ለማስተማር የሚያግዝ ኤአይ(AI)፣ ጣፋጭ ታሪኮችን ጨምሮ ለተማሪዎች እያዝናና በማሳወቅ ረገድ የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው በመርሀ ግብሩ ተገልጿል ፡፡

የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን ስራ አስኪያጅ ህብስት አሰፋ እንደተናገሩት በተመደቡበት የስራ ዘርፍ ተሰልፈው ከመጋረጃ ጀርባ ያሉ የተቋሙ ሰራተኞች እና ባለሙያዎች ምስጋና ይግባና ዛሬ ለዚህ በቅተናል ብለዋል።

ተቋማችን እዚህ ለመድረሱ ሚስጥሩ የልጆቻችን ወላጆች ናቸው ያሉት ስራ አስኪያጇ ስላደረጋችሁት ሁሉ ነገር እናመሰግናለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ልጆች የሚማሩበት ፣ ባሕልና ማንነታቸውን የሚጠብቁበት ፣ ሀገራቸውን የሚረዱበት መተግበሪያ የብዙ ጥረትና ድካም የስኬት ዉጤት ነው።

መስራቾቹ ቢኒያም ከበደ ፣ ህብስት አሰፋና እንዲሁም ለኢትዮጵያ ልጆች ህልውና አብረው የደከሙ ሁሉ በፕሮግራሙ ታዳሚያንና ወላጆች አድናቆትና ምስጋና ሲቀርብላቸዉ ነበር ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን የመከላከያ ስምምነቶችና የፖለቲካዊ ድጋፎች

በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ስጋት ተከትሎ፣ ጣሊያን ለባህረ...

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ”ንዋይ” የተሰኘ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች...

የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ እንግልት እየዳረገ ነው

በአዲስ አበባ እና በልዩ ልዩ የክልል ከተሞች የሚስተዋለው የነዳጅ...

ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት ሀዘናቸውን ገለጹ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም...