የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡደን ደማቅ ሽኝት ተደረገለት

Date:


በናይጄሪያ አቡከታ ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፉት የአትሌቲክስ ልዑክ ቡድን በቼክኢን ሆቴል ደማቅ ሽኝት ተደርጎለታል ።

የልዑክ ቡድኑ መሪና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል
ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ እና የቴክኒክ ቡድን መሪ አቶ ጊዜ አድነው ስለነበራቸው የልምምድ ቅደመ ዝግጅታቸውን ቆይታ በስፋት አብራርተዋል ።

በተጨማሪም አትሌቶችን በመወከል አትሌት እየሩሳሌም አማረ እና አትሌት ሳሙኤል ገ/ሀዋሪያ ስለ ልምምዳቸውን አንስተው የተናገሩ ሲሆን ኢንስትራክተር መሠረት መንግሥቱ አሰልጣኞችን በመወከል የተሰጣቸውን አደራ እንደሚወጡ ተናግሯል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና አቃቤ ነዋይ ወይዘሮ አበበ ዮሴፍ ፌዴሬሽኑ በኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል የዕድሜ ምርመራ ለ88 አትሌቶች ያደረገ ሲሆን 28 አትሌቶች ከ20 ዓመት መሆናቸውን መረጋገጡ አንስተው፣ፌዴሬሽኑ አሁንም ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በዕድሜ ተገቢነት ጉዳይ ላይ አበክረው እንደሚሰራ በመጠቆም፣ለልዑክ ቡድኑ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ መከዩ መሀመድ
ኢትዮጵያ በተለይም በአትሌቲክሱ ዘርፍ ለአፍሪካ ኩራት መሆኗን አንስተው አሁን አገር ወክላችሁ የምትሄዱ አትሌቶች እንደነ ሀይሌ እና ቀነኒሳ የአገራቹን ሰንደቅ አላማ ከፍ እንድታደርጉ እመኛለሁ በማለት መንግስት የማዘውተሪያ ስፍራ ፣የትራክ ችግር ለመፍታት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑንና በቀጣይ ጥቂት ቀናት ችግሩ እንደሚቀረፍ በትጋት እየተሰራ መሆኑን በስፋት አብራርተዋል ።

ሚንስትር ዴኤታው በመጨረሻም ለልዑክ ቡድኑ መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ የሰንደቅ አላማ ርክክብ አድርጓል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አበባ ዮሴፍ ፌደሬሽኑ ለዓመታት የነበረበትን የእድሜ ተገቢነት ችግር ለመቅረፍ፤ በርከታ ሥራዎች እየሰራ እንደሚገኝ እና በናይጄሪያ በሚደረገው መድረክም የሚሳተፉ አትሌቶች በትክክለኛው መንገድ የተመረጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ልዑክ ቡድኑ ሰኞ ወደ ናይጄሪያ አቡኩታ ያመራል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...

በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ...

ንግድ ባንክ “ስታርፔይ” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ሥርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ...

በኢትዮጵያ በካንሰር ከሚያዙ ሕፃናት መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት ህክምና አያገኙም

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በካንሰር ከሚጠቁ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ...