እንደ ኦፕታ መረጃ ዛሬ ቼልሲ ከፒኤስጂ የሚገናኙበት የክለቦች ዓለም ዋንጫ ፍጻሜ በእንግሊዝ እና በፈረንሳይ ክለቦች መካከል ለመጀመርያ ጊዜ የሚደረግ የፍጻሜ ጨዋታ ነው፡፡
ለመጀመርያ ጊዜ 32 ቡድኖችን ያሳተፈው እና በአዲስ የጨዋታ ቅርጽ የተደረገው የክለቦች ዓለም ዋንጫ
ዛሬ ቼልሲ ከፒኤስጂ በሚያደርጉት ፍጻሜ ይጠናቀቃል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሚትላይፍ ስቴዲየም የሚደረገው የዋንጫ ጨዋታም ትልቅ ግምት አግኝቷል፡፡
ሁለቱም ቡድኖች በዚሁ አመት የአውሮፓ ውድድሮችን አሸንፈው የመጡ ናቸው፡፡
