የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን በረራ ጀመረ

Date:


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን የበረራ አገልግሎት ዳግም ጀመረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን የሚያደርገውን በረራ ከጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዳግም ማስጀመሩን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ወደ ፖርት ሱዳን ከጥቅምት 5 ቀን  ጀምሮ በቀን አንድ ጊዜ በረራ እንደሚያደርግ ገልጾ በቀጣይ ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ግን በረራዎቹን በቀን ወደ ሁለት ጊዜ እንደሚያሳድግ ጠቁሟል።

በሱዳን ጦር ሰራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF) መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰበት ሚያዚያ 2015 ወዲህ የሱዳን መንግሥት ዋና ከተማዋን ካርቱምን በመልቀቅ አገሪቱን ሲያስተዳድር የቆየው በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ፖርት ሱዳን ከሚገኝ ጊዜያዊ መቀመጫው እንደነበር ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ፖርት ሱዳን ተከታታይ በረራዎችን ሲያደርግ የነበረ ሲሆን ከወራት በፊት በሀገሪቱ እንደገና ባገረሸው ግጭት ሳቢያ ወደ ፖርት ሱዳን ሲያደርግ የነበረውነ በረራ ለማቋረጥ ተገዶ ቆይቷል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...