የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንደሚያገኝ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ገለጸ

Date:

ግንቦት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ኢትዮጵያ የባሕር በር አስፈላጊነት ለድርድር የሚቀርብ አይደለም ሲሉ በትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር፣ የማሪታይም ባለሥልጣን የሎጀስቲክና ትራንስፎርሜሽን ዳይሬክተር አቶ ወርቁ ለማ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

የባሕር በር ያላቸውና የሌላቸው ሀገራት በዓለም አቀፍ መድረክ ያላቸው ተሰሚነት እኩል አለመሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ኢትዮጵያ የባሕር በርን ለማግኘት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ዕድሎቿን እየተጠቀመች እና በቅርቡም ምላሽ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

“ኢትዮጵያ የባሕር በርን ማግኘቷ ኢኮኖሚን ለማሳደግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን ያስችላታል” ሲሉም ተናግረዋል።

በወጪና ገቢ ምርቶች ላይ የሚያጋጥመውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብም የባሕር በርን የማግኘት ጉዳይ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ጥያቄ ለማቅረብ የሚያስችሏት በርካታ ምክንያቶች እንዳሏትም አቶ ወርቁ አክለዋል።

“ጂኦ-ፖለቲካል ተፈጥሮ፣ ታሪካዊ እውነታ፣ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ዓለም አቀፍ ሕጎች እና የደህንነት ጉዳይ ከምክንያቶቿ ይጠቀሳሉ” ብለዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም፤ “መንግሥት ከ30 ዓመታት በላይ አይነኬ የነበረውን የባሕር በር መብት ጥያቄ አሁን በግልፅ በማንሳት መጠነ ሰፊ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል” ያሉ ሲሆን፤ “ሕዝቡም በመሉ ልቡ ተቀብሎ የሚያምንበት ነው” ሲሉ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መብት በሰላማዊ መንገድ ለማሳካት ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኝ የሁሉንም ድጋፍ እንደምትፈልግ አሳስበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...