
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ(ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከአውሮፓ ኅብረት የግሉ ዘርፍ፣ የንግድ፣ ኢኮኖሚ እና አካባቢያዊ ትስስር ጉዳዮች ፕሮግራም ኦፊሰር አድሪያን ካኖ ጉሬሮ ጋር ተወያዩ፡፡
ሁለቱ አካላት በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን ምክር ቤቱ በሴቶች የቢዝነስ አመራር፣ በቻምበር የዲጂታይዜሽን ስርዓት፣ በቢዝነስና ሰላም፣ በአቅም ግንባታ፣ በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም መጎልበት እንዲሁም በወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ዙሪያ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑን ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ ኢኮኖሚያዊ ስራዎች አስፈላጊውን እገዛ እያደረገ ሲሆን ከምክር ቤቱ ጋርም የሚሰሯቸውን ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሚስተር አድሪያን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በፊትም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከአውሮፓ ኅብረት ጋር በመተባበር በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸው ተጠቁሟል፡፡