የቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ግንባታ በ510 ሚሊየን ብር ሊካሄድ ነው

Date:

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ከ510 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የቃሊቲ ወደብና ተርሚናልን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር ተፈራርሟል።

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) እንደተናገሩት የቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ለአገልግሎት ሰጪዎችም ሆነ ለተጠቃሚዎች ምቹ አይደለም። በመሆኑም በስምምነቱ መሰረት ፕሮጀክቱ በወቅቱ እንዲጠናቀቅና ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የቃሊቲ ወደብና ተርሚናልን የግቢ ውስጥ መንገድ እና የኮንቴይነር ተርሚናል ለማሻሻል ከ510 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበ ሲሆን፣ ግንባታው በስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...