የኢንጂነሩ ድምጻዊ የሙዚቃ አልበም

Date:

“ቃሊ” የተሰኘው የድምጻዊ እስራኤል በሻዳ  አዲስ አልበም ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም  በድምፃዊው የዩቱብ ቻናልና በሁሉም የዲጂታል መተግበሪያዎች ለአድማጭ እንደሚደርስ ድምፃዊው በዛሬው እለት በቢሾፍቱ ከተማ ፒራሚድ ሪዞርት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

“ቃሊ” አልበም በርካታ አንጋፋና ወጣት የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሣተፉበት ሲሆን 12 ያህል ሙዚቃዎች ተካተውበታል።

ድምጻዊ እስራኤል በሻዳ በ2023  የኦሮሞ ምርጥ አዲስ ድምጻዊ ተብሎ እንደተሸለመ የተገለፀ ሲሆን የኦሮሞ ቱባ ባህሉንና ታሪኩን እንዲሁም ጥበቡን የተካተተበት ይህ አልበም ታላቁ የሙዚቃ ሰው አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ የመጨረሻውን ማስተሪንግ እንደሰራው ተነግሯል።

“ቃሊ” አልበም የፊታችን ግንቦት 23 ሲመረቅ ኮንሰርትም እንደሚዘጋጅ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ አልበም ምረቃ በኃላ ድምፃዊ እስራኤል በሻዳ በአዲስ አበባ ፣ በአዳማ ፣ በድሬደዋ እና በሌሎች ከተሞች የሙዚቃ ዝግጅት እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

ድምጻዊ እስራኤል በሻዳ ከዚህ ቀደም “ናንዬ” በተሰኘው ሙዚቃው ተወዳጅነትን አትርፏል።

ድምጻዊ እስራኤል በሻዳ ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ኢንጂነር ተመርቆ በሞያው ለአመታት እየሰራበት ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...