የትግራይ ሕዝብ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ መስዋዕትነት የሚከፍል አይደለም

Date:

የትግራይ ሕዝብ በቀድሞ የሕወሓት ጥቂት አመራር አባላት የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመታለል መስዋዕትነት የሚከፍል አይደለም ሲሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የትግራይ ሕዝብ የጥቂት ስልጣን ፈላጊ ቡድኖችን ድምጽ እየሰማ ለዓመታት ተጉዟልል፤ ከዚህ በኋላ በሐሰት ፕሮፖጋንዳ የሚታለል የለም፡፡

ሕዝቡ ሐሳቡን በነፃነት መግለጽ የጀመረው የጊዜያዊ አስተዳደር ከተመሰረተ በኋላ መሆኑን በመጥቀስ፤ ሕዝቡ የሰላም አካል መሆኑን የሚያረጋግጥበት መድረክ በየጊዜው ይዘጋጃል ነው ያሉት፡፡

የትግራይ ሕዝብ የተወሰኑ ሰዎችን የስልጣን ጥም ለማርካት መሞት የለበትም ያሉት ሚኒስትሩ፤ የጥቂት ሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት የሚከፈል መስዋዕትነት አይኖርም ብለዋል፡፡
የትግራይ ሕዝብ ዋነኛ አጀንዳ ሰላም መሆኑን ገልጸው፤ በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት ላይ በጋራ መምከር ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...