የኮሶ በሽታ ከተለያዩ የትል በሽታዎች ኣንዱ ነው። ከሰው ኮሶ በሽታዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የታወቀው ሕዋስ ቲንያ ሳጂናታ ይባላል። በሽታው ሰውን የሚይዘው ያልተመረመርና ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰለ የከብት ሥጋ በመብላት ሲሆን በሽታውን የሚያስከትለው እንቁላል ጥሬ ሥጋ ውስጥ የሚቀመጥና ያለማጉሊያ መሣሪያ በዓይን የማይታይ ነው። አንድ ሰው የኮሶ እንቁላል ያለበትን ጥሬ ስጋ ከበላ በኋላ እንቁላሉ ይፈለፈልና አንጀት ላይ ጭንቅላቱን በመትከል ከአንገቱ ማደግ ይጀምራል። የኮሶ ትል ርዝመት ከሰው ቁመት ሊበልጥ ይችላል። በቂ እድሜ ካገኘ በኋላ ብዙ እንቁላሎች ያሉት የሚቀነጠሱ ጉማጆች ከሰገራ ጋር ወይም ለብቻቸው ይወጣሉ።
የኮሶ መድኃኒት ተወስዶ ትሉ ጭንቅላቱ ከእንጀት ተነቅሎ ወይም ሲወጣ ኣሻረኝ ይባላል። የኮሶው መድኃኒት ኮሶውን ከኣንጀት ፈንቅሎ ካላወጣው ግን እንደገና ከኣንገቱ በመጀመር ያድግና ሌላ ጉማጆችን መልቀቅና ማሳየት ሲጀምር ኮሶ ታየኝ ይባላል። ስለዚህ አንድ ሰው ኮሶ ሲታየው ትሉን ከጭንቅላቱ ፈንቅሎ የሚያወጣ መድኃኒት መውሰድ ኣለበት። አንድ ጉማጅ ውስጥ ብዙ የኮሶ እንቁላሎች ስላሉት አንድ ኮሶም ብዙ ዓመታት ስለሚኖር ብዙ ሺህ እንቁላሎች ይኖራሉ። አንድ ሰው ሰገራውን ሜዳ ላይ ሲወጣ ጉማጁ ፀሓይ ሲሞቀው ይፈነዳና ብዙ ሺህ እንቁላሎቹ ሳር ላይ ይረጫል። ከብቶች እንቁላሎቹን ከሳሩ ጋር ሲበሉ ተፈልፍለው ሆድ ዕቃቸውን ስርስረው የከብት ስጋ ውስጥ ተቀምጠው ጥሬ ስጋ የሚበላ ሰው እስኪመጣ ይጠብቃሉ። የግዴታ ሰገራ ሜዳ ላይ መውጣት ካስፈለገ ትንሽ ጉድጓድ ቆፍሮ ከእዚያ ሰገራውን በኣፈር መሸፈን እንቁላሎቹ እንዳይፈለፈሉ ይጠቅማል። ኮሶ የሰው እንጂ የሌሎች እንሰሳት በሽታ አይደለም። ሥጋን ማብሰል የኮሶውን እንቁላል ይገድለዋል። የኮሶ እንቁላል ያለበትን የከብት ሥጋ ለሁለት ሳምንታት ፍሪዝ ማድረግም ይገድላቸዋል። መከላከል እንዳለ ሆኖ በሽታውን ከስሩ ነቅሎ ለማጥፋት ፕራዚኳንቴል (praziquantel) ወይም ደግሞ ኒክሎሳማይድ (Niclosamide) የተባሉ መድኃኒቶችን መውሰድ ይገባል። ካልተከላከልነው ግን በሽታው ቢጠፋም መልሶ ሊይዘን ይችላል።
የትርፍ አንጀት ሕመም
የትርፍ አንጀት በሽታ ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው የትርፍ አንጀቱ በሰገራ፥ በሌላ እንግዳ አካል ወይም በካንሰር ስዘጋ ነው። የትርፍ አንጀት ሲቆስል ስለሚያብጥ የሚዘጋው በቁስለትም ሊሆን ይችላል። በሽታው የሚከሰተው ባክተሪያዎች የትርፍ አንጀትን ግድግዳ ሲወሩትና ሲያቆስሉት ነው።
ምልክቶቹ፡-
የትርፍ አንጀት በሽታ ምልክቶች በእርግጥ የህመሙን ስሜት ቦታ ለማመልከት አስቸጋር ቢሆንም በእምብርት አከባቢ የህመም ስሜት መሰማት፥ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፥ የሆድ ህመም እንደጀመረ ማቅለሽለሽና ማስታወክ፥ ከ38 እስከ 39.2 ድግር ሲሸልስ የሚደርስ የሰውነት ሙቀት መጨመር፥ ሽንት በሚሸናበት ጊዜ የህመም ስሜት መሰማት፥ እና ተቅማጥ ጥቅቶቹ ናቸው።
ምርመራው፡-
የትርፍ አንጀት በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለዋወጠ ስለሆነ ምርመራውን ለማካሔድ እጅግ አስቸጋር እየሆነ ነው። በሽታውን ለመመርመር ብዙ ጊዜ የጤና ባለሙያው ምልክቶቹን በማየት፥ የጤንነት ሁኔታውን ከበሽተኛው በመጠየቅና የሆድ ምርመራ በማድረግ ሊያውቅ ይችላል። ምርመራውም የህመሙን ሁኔታ ለማወቅ በሽተኛውን የሚያመው አከባቢ ጫን በማለት የአካላዊ ምርመራ በማድረግ፥ የበሽተኛው ሰውነት መመረዙን የሚያሳዩ ከፍተኛ ነጭ የደም ሴል በብዛት መኖሩን የደም ምርመራ በማድረግ፥ እና የሽንት ምርመራ በማድረግ ማወቅ ይቻላል።
መከላከያው፡-
በአብዛኛው ከፍተኛ የሆነ ቃጫነት ያለበትን ምግብ በብዛት በማይመገቡ አገሮች ውስጥ የትርፍ አንጀት በሽታ አናሳ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ። ይህ ለምን እንደሆነ በእርግጥ አይታወቅም፤ ሆኖም ግን እንደ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉት ከፍተኛ ቃጫነት ያለበት ምግብ ሰገራችንን ስለሚያለሰልሰው፥ በትርፍ እንጀት ሄደው መወተፍን ስለሚቀንስ ሊሆን ይችላል። ቃጫነት ያለባቸው ምግቦችም ሁሉም የአገዳ እህሎች፥ ስንዴ፥ ሩዝ እና ፓስታ፥ እንደ ካሮት ያሉ የሥራሥር አትክልቶች፥ እና ፍራፍሬዎች ናቸው። እነዚህን ምግቦች ማዘውተር የትርፍ አንጀት በሽታን ለመከላከል ይጠቅማል::
የአፍ ዉስጥ ፈንገስ (Oral Candidiasis)
የምላስ ነጭ መሆን መንስኤው ካንዲዳ ከሚባሉ ዩስት ሲሆን የምላስ መንጣት ደግሞ ካንዲዲያሲስ ይባላል፡፡ ካንዲዳ ለሰውነታችን እጅግ ጠቃሚ ናቸው ነገር ግን ከመጠን በላይ በሚያድጉበት ወቅት ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራሉ።
መንስኤዎቹን፡-
• የበሽታ የመከላከል አቅም መዳከም
• ለረጅም ጊዜ አንቲባዮቲክ መድሀኒቶች መጠቀም
• የወሊድ መቆጣጠሪያ መውሰድ
• ኢንሱሊን (የስኳር በሽታ መድሀኒት)
• እርግዝና መኖር
• ደካማ የአፍ ጤንነት አጠባበቅ
• የአፍ መድረቅ
• ትምባሆ መጠቀም
• አልኮል መጠቀም
• ጣፋጭ ምግቦችን መውሰድ
ምልክቶቹ፡-
• እንደ አይብ የመሰለ ነጭ ነገር ምላስ ላይ መታየት
• የምግብ ጣእም አለመለየት
• በእጅ በሚነኩበት ጊዜ መድማት
• በአፍ ዙሪያ መቅላት
• ለማኘክ ፣ለመዋጥ መቸገር
የቤት ውስጥ ህክምናዎች፡-
በደቃቅ ጨው ለአንድ ደቂቃ በጥርስ ብሩሽ ምላስን መቦረሽ፡፡ ከዚያም በሙቅ ውሀ በደንብ መታጠብ፡፡ ሁለት ጊዜ በየቀኑ ይድገሙ እና በሳምንት ውስጥ የሚፈልጉትን ውጤቶች ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም ለብ ያለ ውሀ ውስጥ 1 የሻይ ማንኪያ ጨው ይቀላቅሉ፡፡ በዚህ የጨው ውሀ አፍን በመሙላት ይጉመጥሞጡ። ሾርባ ላይ እሬት (አሎቬራ)በመጨመር በአፍ ውስጥ መጉመጥመጥ እንዲሁም 1 ማንኪያ የአሎቬራ ጭማቂ ይጠጡ ይህን መድሀኒት በየቀኑ ማድረግ ለ 2 ሳምንታት ያህል ማድረግ፡፡
የዶክተር አለ
